1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱምሳ ላሚ የበጎ አድራጎት ኮሚቴ ተፈናቃዮች የመርዳት ጥረት

ቅዳሜ፣ ሰኔ 4 2014

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ባቋቋሙት ቱምሳ ላሚ የተባለ የበጎ አድራጎት ኮሚቴ በኩል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች እገዛ እያደረገ ነው። የኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር አሊማ ጅብሪል ብር፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ ብርድ ልብሶችና የንጽህና መጠበቂያዎች እያሰባሰበ ለተፈናቃዮች እንደሚሰጥ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4CZUB
Äthiopien Wollega University
ምስል Hassen Yusuf

የቱምሳ ላሚ የበጎ አድራጎት ኮሚቴ ተፈናቃዮች የመርዳት ጥረት

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች  "ቱምሳ ላሚ" በሚል ስም በተደራጀው የበጎ አድራጎት ኮሚቴ  ወደ 3 ሚሊዩን ብር በማሰባሰብ በጸጥታ ችግር ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ለተፈናቀሉ ዜጎች  ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ድጋፉ የተሰጠውም ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልሎት ስራ በሚያከናውንባቸው ስፍራዎች ሲሆን 10 በሚደርሱ ወረዳዎች ውስጥ የምግብ እህልን ጨምሮ የአልባሳት ድጋፍ ለተወሰኑ ሰዎች ማድረሳቸውን  በዮኒቨርሲቲው የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር አሊማ ጅብሪል ለዲዳቢሊው አመልክተዋል፡፡  ዩኒቨርሲቲው በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ፣በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ እና በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ የማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ተገልጸዋል፡፡

በአምስት የወለጋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የተጀመረው የቱምሳ ላሚ የተባለ ኮሚቴ ከወር  በፊት በአካባቢው የሚገኙ በጸጥታ ችግርና በተለያዩ ምክንያች የተጎዱና የተፈናቀሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማገዝ ወደ ስራ መግባቱን ዩኒቨርሲቲ አመልክተዋል፡፡  በቱምሳ ላሚ በኩል 3 ሚሊዩን ብር የሚሆን ገንዘብ ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ከሌሎች የግል ተቋማትም  በማሰባሰብ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ማድረጉም ተገልጸዋል፡፡ ዶ/ር አሊማ ጅብሪል የቱምሳ ለሚ ሰብሳቢና በዩኒቨርሲቲው የሰቶችና ህጻናት ጉዳይ ኃላፊ ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ በሚያከናውንባቸው ስፍራዎች እና በጥናት የተለዩ ወረዳዎች፤ በምዕራብ ወለጋ ሶስት ወረዳዎች፣ በምስራቅ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋም በተመሳሳይ ባጠቃላይ 10 በሚደርሱ ወረዳዎች ድጋፍ ለማሰባሰበ በተቋቋመው ኮሚቴ በኩል እስካሁን የምግብ እህልና አልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸውን አብራርተዋል፡፡

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሐሰን ዩሱፍ ዩኒቨርሲቲው በወለጋ ሶስት ዞኖች የማህበረሰብ አገልግሎት ስራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ በግምቢ፣ ሻምቡና የዩኒቨርሲቲው ዋና ጊቢ በሚገኝበት ምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ጥናትና ምርምር ከመስራት ጎን ለጎን የማህበረሰብ አገልግሎት በኩል የተፈናቀሉ ማህበረሰብን የዕለት ደራሽ ሰብአዊ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በራሳቸው ፍላጎት ለ2ኛ ጊዜ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በምስራቅና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ የተወሰኑ ቦታዎች የሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች በአካባቢአቸው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና የተዘጉ መንገዶች ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ሀሳብ አቅርቧል፡፡ ለሂኪምና እና ለተለያዩ አገልግሎት መንገዶች ለረዥም ጊዜ በመዘጋታቸው ለችግር መጋለጣቸውን ሲገልጹ ቆይቷል፡፡

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች በጥር ወር 2014 ዓ.ም በማህበራዊ መገናኛ ዜዴ እና በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ዜጎች ወደ 2 ሚሊዩ ብር በማሰባበሰብ ለጊዳ አያና እና ኪራሙ የተባሉ ወረዳዎች ለሚገኙ የተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አድርጓል፡፡ በሁለቱ ወረዳዎች 80ሺ የሚደርሱ የተፈናቀሉ ዜጎች እንደሚገኙም መዘገባችን ይታወሳል 

ነጋሳ ደሳለኝ