ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጆችን አጽድቋል። ምክር ቤቱ ትናንት በተቀመጠው መደበኛ ጉባኤው የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ አዋጆቹን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ዘገባና የውሳኔ ሀሳብ አቅርቦ በዝርዝር ጉዳዮቹ ላይ ከተመከረ በኋላ አዋጆቹ በአብዛኛው ድምጽ ፀድቀው ወደ ተግባር ተገብቷል።
በተለይም የውጪ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የሚፈቅደው የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት የሚያደርገው የጸደቀው የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ በአዎንታዊውም ሆነ በአሉታዊ ጎኑ በብዙ አነጋግሯል። ለመሆኑ ቁጥራቸው ከ30 የተሻገረው አብዛኛው የኢትዮጵያ የግል ባንኮች ከውጪ ልመጣ ነው እየተባለ የሚገኘውን ብርቱ ውድድር ለመቋቋም ዝግጁ ናቸው?