1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዐቢይ የፓርላማ ዉሎ፤ የቀጠለዉ አፈናና ግድያ፤ በትግራይ በረሃብ ሰዎች እየሞቱ ነዉ መባሉ

ዓርብ፣ ሰኔ 30 2015

ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሰፊ አስተያየቶች ከተሰጡባቸዉ ርዕሶች መካከል፤ የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የፓርላማ ዉሎ፤ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የቀጠለዉ አፈና፤ ግድያ እና የነዋሪዎች ሮሮ፤ እንዲሁም በትግራይ በረሃብ እና በተያያዥ ጉዳዮች ሰዎች እየሞቱ ነዉ መባሉ የተሰኙ ርዕሶችን እንዳስሳለን።

https://p.dw.com/p/4TWvY
Äthiopien Stadt Nekemit | Premierminister Abiy Ahmed mit Vertretern der Wollega-Zonen Region Oromia
ምስል Facebook.com/Office PM Ethiopia

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሰፊ አስተያየቶች ከተሰጡባቸዉ ርዕሶች መካከል፤ የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የፓርላማ ዉሎ፤ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የቀጠለዉ አፈና፤ ግድያ እና የነዋሪዎች ሮሮ፤ እንዲሁም በትግራይ በረሃብ እና በተያያዥ ጉዳዮች ሰዎች እየሞቱ ነዉመባሉ የተሰኙ ርዕሶችን እንዳስሳለን።   

ትናንት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ28ኛው መደበኛ ጉባዔ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፓርላማ አባላት ለተሰነዘሩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከፍተኛ አስተያየቶችን ያስተናገደ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስልጣናቸውን ለጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም ፓርላማውን እንዲበትኑ እና “ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ” የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ መጠየቃቸዉ ካነጋገሩት ነጥቦች አንዱ ነዉ። ዶ/ር ደሳለኝ ጥያቄውን ያቀረቡት “ብልጽግና ፓርቲ መራሹ መንግስትም ሆነ ፓርላማው”፤ ኢትዮጵያ “ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር ወይም ፖለቲካዊ deadlock ማውጣት ስለማይችሉ” በመሆኑ መሆኑን ተናግረዋል። የፓርላማ አባሉ በሀገሪቱ ተስተውሏል ላሉት “ሁለንተናዊ ሀገራዊ ምስቅልቅል፣ ቀውስ፣ ውድመት እና ሀገራዊ መክሸፍ” የመንግስትን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን “የወደቀ” ያሉትን አመራር ዋነኛ ተጠያቂ አድርገዋል።  ዶ/ር ደሳለኝ ፤ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የነበሩ እና ያሉ “ጦርነቶችን” ጠቅሰዋል። 

Symbolbild Soziale Netze
የማህበራዊ መገናኛ ዘደዎች ቅኝት ምስል Axel Heimken/dpa/picture alliance

በርካታ አስተያየት ሰጭዎች በሰጡት አስተያየት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔን እናመሰግናለን ፤ ፈጣሪ ይጠብቅህ ሲሉ ነዉ አስተያየታቸዉን ያስቀመጡት። አንጀት አርስጥያቄ ሲሉም አስተያየታቸዉን የሰጡ ጥቂቶች አይደሉም። ጉዱ ካሳ የተባሉ አስተያየት ሰጭ፤ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር በቅጡ ያውቁታል ብየ አላምንም ነበር አሁን ግን የተረዱት መሆኑን ለመገንዘብ ችያለው፤ ይላሉ።

በሪሶ ገመቹ በሪሶ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ፤ በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራማችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዛፎችን መትከል ተችሏል። ይህ የሚያሳየን ህዝባችን በትብብር እና በአንድነት ከተነሳ ተአምራዊ ስራ መስራት እንደምንችል ነው። 

ደረጀሙላትየተባሉ አስተያየት ሰጭ ፤ ለየት አይነት አስተየያየት ነዉ የሰጡት። ሀገር አፍራሽ እና ተላላኪ ባንዳ ስለ ሀገር ተስፋም ሆነ ሀገር ልማት ምንም ነገር አይታየዉም። እንደዚህ አይነት mentality ያላቸዉን ሰዎች፤ ሀገር ወርቅ ብታነጥፍላቸዉም ምንም ምስጋና አይኖራቸዉም፤ ብለዋል።

በትናንቱ የፓርላማ ዉሎ የፓርላማ አባሉ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አነሳሽነት እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ደግፈው አስተያየት ሰጥተዋል። "ዶ/ር አብይ አህመድ ታማኝ፣ ባለአደራ፣ selfless ሰው በመሆንዎ እንኮራቦታለን" ሲሉ  ምስጋናን አቅርበዋል።

ኃይሌ ሃሳና የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ፤ ያለዉን እዉነታ በመመሰከርህ አከብሮት አለኝ ብለዋል። አዲስ ወርቁ የተባሉ በበኩላቸዉ „እዉነትም አሸብር የወከሎት ህዝብ ድምጽን አፍነዋል። ይህ የአደርባይነት ጥግ ነዉ ሲሊ ነዉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል።

ጌቱ አባንዲ የተባሉ አስተያየት ሰጭ፤ ሰላም መተማመንን ይፈልጋል፣ ሰላም መከባበርን ይፈልጋል፣ ሰላም ይቅርታን ይፈልጋል፣እንደምናየው የጥላቻን ዘር እየተዘራ፣ ጥቃትን ስድብን እየተረጨ፤ የሰላምን ፍሬ መግኘት አይቻልም። ሰላምን ዘርተን ነው፤ ስላምን ማጨድ የሚቻለዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል"

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በሚያዝያ የጀመሩት የሰላም ንግግር ለኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ችግር መፍትሔ ያበጃል የሚል ተስፋ ተጥሎበት ነበር። የሁለቱ ወገኖች የሰላም ንግግር የቆመ ሲሆን እስካሁን በተጨባጭ የታየ ለውጥ የለም። አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች እገታ ግድያ እንደቀጠለ ነዉ። የነዋሪዎች እሮሮም አልቆመም።

ኦሮሞስ ቫኑግራድ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ፤ የዚህ እልባት የሚገኘዉ በመንግሥት እጅ ላይ ነው።  የኦሮምያን መዋቅሮች አፍርሶ በአዲስ ማደራጀት ነዉ ዋናዉ መፍትሄ፤ ሲሉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል።

 Kamashi town in Benishangul Gumuz region Ethiopia
ካማሺ ከተማ ቤኒሻንጉልምስል Negassa Dessalegn/DW

ሸኔ ማለት እኮ የሚሉት አስተያየት ሰች እዮብ አለምነህ ይባለሉ። ሸኔ ማለት እኮ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ከህግ ውጭ የሆነ ጉዳዩን  የሚያስፈፅምበት ማሽን ነው። የማያስፈልገዉን ሰው የሚያስወግድበት፣ ገንዘብ ሲያጣ እያሳገተ ብር የሚቀበልበት፣ ያኮረፈ ፓለቲከኛን የሚያግትበ ፣ ከባለሀብት ብር የሚቀፍልበት፣ ሙስና የሚያስፈፅምበት በአጠቃላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድብቅ ጉዳይ አስፈፃሚ ነው። ታዲያ ከማን ጋር ነዉ የሰላም ንግግር የምትሉት? ብለዉ አስተያየታቸዉን በጥያቄ ይቋጫሉ።

ታደለ ፈቃደ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ፣ ኦነግ ሸኔም በለው ሌላ...ህወሃት በህዝባዊ አመፅ ስልጣንን በኦሮሞ የተቀማችበትን ለመበቀል የሳደገችዉ ኃይል ነው።  አላማውም ስልጣንን መመለስ ባይሳካ እንኳን ህዝቡንና ክልሉን ማውደም ነው።  ስልጣን ላይ ያለውም ሆነ በሌላኛው ወገን ተዋጊው ማን እንደሆነ ለመረዳት ባይከብዳቸውም በግለሰብ ደረጃ የሁለቱም ጎራ መሪዎች ዘርፈው እየበሉ ስለሆነ በቀላል አያቆሙትም። ህዝቡ ግን በአጥንቱ እስኪቀር ድረስ ይግጡታል፤ሲሉ አአስተያየታቸዉን ጽፈዋል።

ዳንኤል አባተ የተባሉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸዉ፤ ኦሮሚያ ለሰው ልጅ ሲኦል ሆናለች። መጀመሪያ ላይ  ችግሩ ለተወሰነ ብሔር ብቻ መስሎዋቸው የተደሠቱ ሁሉ አሁን እኩል እየተሰቃዩ ነው። ችግሩ የጋራ ስለሆነ ለመፍትሄውም በጋራ መቆም ነው ሲሉ አስተያየታቸዉን ጽፈዋል።

ዳንኤል መኮንን አባተ፤ መፍትሄ ከብፅግና ለማግኘት ሰዉ ልጠብቅ ካለ ሞኝነት ነው።  እንዳውም ብልፅግና ጦፍቶ ሌላም ቢመጣ ያው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥርጣሬ እንዲኖረዉ አድርጓል፤ መበታተን  የማይቀር ነው የሚል ግምት እየመጣነዉ።  ምንአልባት ኢትዮጵያ አንድ ከፈጣሪ የተላከ መሪ ካገኘች ሊያስተካክልው ይችላል። አለበለዝያ ግን፤ እንኳንስ የራሱ ወታድር የሻእብያ ወታድርን ኣስገብቶ ወገኑን ያስጨፈጨፍ ብቸኛው ከሀዲዉ ብልፅግናን ማመን እና ጥሩ ይሰራል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነዉ፤ ሲሉ አስተያየት ጽፈዋል።

ትግራይ ዉስጥ በረሐብ   የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ የክልሉ አስተዳደር በያዝነዉ ሳምንት አስታዉቋል። የትግራይ አደጋ መከላከል ኮምሽን እንዳለው፣ በተለይ ለጋሽ ድርጅቶች ይሰጡት የነበረዉን የምግብ ዕርዳታ  ከቋረጡ ወዲህ በሦስት የትግራይ ዞኖች ከ700 በላይ ሰዎች በረሃብ እና በተያያዥ ችግሮች ህይወታቸዉን አጥተዋል። ወደ ትግራይ የተቋረጠው የምግብ እርዳታ አቅርቦት በአፋጣኝ እንዲቀጥልም ከተለያዩ አካላት ጥሪ ቀርቧል።

Äthiopien Mekele | Hilfssammlung für Kriegsopfer in Tigray
ለትግራይ እርዳታምስል Million Haile Selassie/DW

ዓለም ከበደ የተባሉ የፌስ ቡክ ተከታታይ ምስኪኑ የትግራይ ህዝብ የእርዳታ እህል ሊደርሰዉ ይገባል። የኢትዮጵያ መንግሥት ብሎም የሃገሪቱ ህዝብ ለምስኪኑ ህዝብ እርዳታ እንዲደርስ ጫና መፍጠር አለበት ብለዋል።

ራሄል ቃል የተባሉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸዉ፤ ዓለም አቀፍ የርዳታ ሰጭ አካላት፤ ለህዝቡ ርዳታዉን ለማድረስ አፋጣኝ ርምጃ መዉሰድ ይገባቸዋል። ይህ የርዳታ እንቅስቃሴ ነገ ዛሬ ሳይል መጀመር ይኖርበታል። የርዳታ እህሉ እንዳይሰረቅም ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደተፈገበት ሊደርስበት የሚችልበትን ዘዴ በጥንቃቄ ማየት አለባቸዉ ሲሉ አስተያየትጽፈዋል።  

ተመስገን መስፍን የተባሉ፤ ቆይ የአማራ እና የትግራይ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚደረገው መቼ ነው? ሲሉ ያጠይቃሉ።  የአማራ እና የትግራይ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚደረገው መቼ ነው?  አማራ እያለለት ተጋሩ ለምን ይራባል? የሚያስታርቅ ሽማግሌ የሀይማኖት አባት ግን እስካሁን ይጥፋ ? ሲሉ በጥያቄ ምልክት አስተያየታቸዉን ቋጭተዋል።

ሙሉዉን የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጥንቅር የድምጽ ማድመቻ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሠ