Tesfalem Waldyes Eragoዓርብ፣ መስከረም 5 2010የዜና መጽሔት አምስት ጉዳዮች ይዳስሳል፡፡ ቀዳሚው የሶማሌ ክልል በአወዳይ ከተማ ለተገደሉ የክልሉ ተወላጆች ያከናወነው የቀብር ስነ-ስርዓትን የተመለከተ ዘገባ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በወቅታዊ የሀገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በመኢአድ ጽህፈት ቤት የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይከተላል፡፡ በመጪው እሁድ ስለሚካሄደው ስለቅማንት ህዝበ ውሳኔ የተጠናቀረ ዘገባ አለን፡፡ የጀርመን የምርጫ ዘመቻን አስመልክቶ ከባልደረባችን ማንተጋፍቶት ስለሺ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገናል፡፡ በስተመጨረሻም የምያንማር ሮሒንጃዎች ላይ እየደረሰ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ እንመለከታለን፡፡