የጀርመኑ መራሔ መንግሥት የቻይና ጉብኝት
ዓርብ፣ ጥቅምት 25 2015ማስታወቂያ
ዛሬ በቻይና የመጀመርያ ጉብኝታቸዉን የጀመሩት የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ የቻይና ርዕሰ መስተዳድር እና የሕዝባዊት ቻይና ፓርቲ መሪ ዢ ጂንፒንግ ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸዉ። ሁለቱ ባለሥልጣናት መዲና ቤጂንግ በሚገኘዉ በሕዝባዊት ቻይና ትልቅ አዳራሽ በሚያካሂዱት ዉይይት በዋናነት ስለሃገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ስለዩክሬን ጦርነት እንዲሁም በታይዋን ጉዳይ በተፈጠረዉ ውጥረት ላይ ያተኩራሉ ተብሎ ይታመናል። ዢ ጂንፒንግን የሕዝባዊት ቻይና ፓርቲ መሪ ሆነው በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ከምዕራቡ ዓለም ሃገራት ለመጀመርያ ጊዜ ያገኝዋቸዉ ዛሬ የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ መሆናቸዉ ነው። ቻይና አሁንም ኮቪድ 19ን ሙሉ በሙሉ ከሀገሪቱ ለማስወገድ ጥረት እያደረገች ሲሆን፤ የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ጉብኝትም ጥብቅ የኮሮና ጥንቃቄ ርምጃዎች እየተወሰደ ባለበት ጊዜ መሆኑን ከስፍራዉ የደረሰዉ ዜና ያሳያል።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ