1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀነራል ታደሰ ወረደ መግለጫ

ዓርብ፣ ጥቅምት 18 2015

ወቅታዊ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ያነሱት ጀነራል ታደሰ ጠላት ያልዋቸው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሰት ጦሮች ከሽረ በተጨማሪ አክሱምና ዓድዋን መቆጣጠራቸውን ገልፅዋል። "የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሠራዊት ዓድዋን ተቆጣጥረዋል። ከዓድዋ ወደ ሐውዜንና ተንቤን ለመቀጠል እቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ነው"ያሉት ጀነራሉ ይሁንና "መቀጠል አልቻሉም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4IobQ
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

የጀነራል ታደሰ ወረደ መግለጫ


የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስት ጦሮች ከሽረ በተጨማሪ አክሱም እና ዓድዋ ተቆጣጥረው ወደ ሌሎች አካባቢዎች የመግባት እንቅስቃሴ  ቢያደርጉም ታጣቂ ሐይላቸው የሁለቱ ሀይሎች ወታደራዊ እንቅስቃሴ መግታቱ የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች ዋና አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ። ጀነራሉ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትላንት ማታ በሰጡት መግለጫ ጦርነቱ አሁንም በተለያዩ ግንባሮች ተጠናክሮ እየቀጠለ ነው ብለዋል። 
የትግራዩ ጦርነት ዓለምአቀፍ ሕጎች የጣሰ፣ ንፁሀንን ዒላማ ያደረገ፣ ዘግናኝ ሁነቶች እያስተናገደ ሆኖ እየቀጠለ ስለመሆኑ የገለፁት «የትግራይ ሀይሎች» አዛዥ መሆናቸው የተገለጸው ጀነራል ታደሰ ወረደ ጦራቸው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሀይሎች እየገጠመ ድል እያስመዘገበ ስለመሆኑ ትላንት ማታ በወቅታዊ የጦርነቱ ሁነቶች ዙርያ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ወቅታዊ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ያነሱት ጀነራል ታደሰ ወረደ ጠላት ያልዋቸው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሰት ጦሮች ከሽረ በተጨማሪ አክሱም እና ዓድዋን መቆጣጠራቸውን ገልፅዋል። "የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሠራዊት ዓድዋን ተቆጣጥረዋል። ከዓድዋ ወደ ሐውዜንና ተንቤን ለመቀጠል እቅድ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ነው" ያሉት ጀነራል ታደሰ ይሁንና "መቀጠል አልቻሉም ብለዋል። 
በኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ተወካዮች መካከል በደቡብ አፍሪካ እየቀጠለ ካለው የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ አስተያየታቸው የሰጡት ጀነራሉ የሚገኘውን ውጤት ተመልክተው ለሰላም ይሁን ጦርነት ጦራቸው ዝግጁ መሆኑ ገልፀዋል። "የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦርን የሚያስወጣ ከሆነ ለሰላማዊ ንግግር ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል" የሚሉት የታጣቂዎቹ አዛዥ ጀነራል ታደሰ ወረደ ግን ደግሞ የሰላም ተስፋ ብቻ ሳይሆን ላይሳካ የሚችልበት አጋጣሚ ስለመኖሩ አንስተዋል። " ምርጫቸው ጦርነት ከሆነ ጦርነቱ ይቀጥላል። ሰላማዊ መፍትሔ የሚመጣበት ዕድል ካለ እንቀበላለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ