1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርት

የጥበብ ልጆች ክፍል 03 ርዕስ - «ልጅነቴን አትንጠቁኝ»

ብሩክታይት ጥጋቡ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 7 2017

ልጆች ከትምህርት ርቀው ለረዥም ሰዓታት ከአቅማቸው በላይ እንዲሰሩ ሲገደዱ ብታዩ እናንተስ ምን ታደርጋላችሁ? «የልጆችን ደህንነት በማረጋገጥ እናንተም ጀግኖች መሆን ትችላላችሁ!»ይላሉ የጥበብ ልጆች

https://p.dw.com/p/4ng3d

ሰዎች ችግር ሲያጋጥማቸው የጥበብ ልጆች ልዩ ችሎታቸውን ይዘው ለእርዳታ ከተፍ ይላሉ! 
ጠንካራዋ ሴት ፍትህ አስገራሚ ፍጥነቷን እና ኃይሏን፣ ባለረቂቅ አእምሮዋ ሴት-  ትግስት ምክንያታዊነቷንና የፈጠራ ክህሎቷን፤ ልብ አዋቂዋ ሴት ፍቅር- የሰውን ስሜት በጥልቀት መረዳቷንና አደጋ የመከላከል አቅሟን! እነዚህ ሶስት ሴቶች አንድ ላይ ሲመጡ ኃይላቸው እጥፍ ድርብ ስለሚሆን ማንም ሊያስቆማቸው አይችልም! #የጥበብልጆች