1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈረንሳይና የጀርመን ግጥምያ

ሐሙስ፣ ሰኔ 30 2008

የአዉሮጳ የእግር ኳስ ሻምፒዮና የግማሽ ፍፃሜ ፉክክር ዛሬም ይካሄዳል። ትናንት ፖርቱጋል ዌልስን ሁለት ተምንም ከሸኘች በኋላ የጀርመን እግር ኳስ አፍቃሪዎች ብሔራዊ ቡድናቸዉ ግብ አዳኙ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሚገኝበት ቡድንን መጋፈጡን በማሰብ ሙሉ ድጋፋቸዉን ለመስጠት በርከት ብለዉ ወደ ፈረንሳይዋ ማርሴል ከተማ መጓዛቸዉ ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/1JLLZ
Frankreich Testspiel Deutschland vs. Frankreich
ምስል picture alliance/Pressefoto Ulmer/M. Ulmer

ይህ ጨዋታ ለቡድኑ ወሳኝ ነዉ የሚሉት የእግር ኳስ ወዳጆች የዩሮ 2016 አስተናጋጇ ፈረንሳይም ዋንጫዉን እዚያዉ ለማስቀረት ታጥቃ መነሳቷን እየተናገሩ ነዉ። የዶቼ ቬለ ሳምንታዊ የስፖርት አዘጋጅ ማንተጋፍቶት ስለሺ የሁለቱ ቡድኖች ዝግጅት ምን እንደሚመስል ጠይቀነዉ ነበር።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ