ፖለቲካሰሜን አሜሪካ
የፕሬዚደንት ጆ ባይደን ንግግር ከምርጫ ሽንፈት በኋላ፥ ቃለ መጠይቅ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 28 2017ማስታወቂያ
ጀርመን ጥምር መንግሥት ለመመስረት የተደረገው ጥረት መፍረሱ በተነገረበት ዕለት ዛሬ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለአሜሪካውያን ንግግር አሰምተዋል ። ንግግራቸው ዴሞክራት ፓርቲያቸው በአሜሪካ ምርጫ ከተሸነፈ በኋላ የመጀመሪያው ነው ።
የዋሽንግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀ የፕሬዚደንቱን ንግግር ተከታትሏል ። ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ዛሬ ባሰሙት አጠር ያለ ንግግር የፓርቲያቸውን የዘንድሮ ምርጫ ሽንፈትተቀብለዋል ። በጥር 12 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በሚኖረው የሥልጣን ሽግግር ወቅትም፦ «ሰላማዊ የኃይል ሽግግር» ይኖራል ብለዋል ።
የፕሬዚደንትነት ምርጫውን ስላሸነፉት ተቀናቃኛቸው የሪፐብሊካን መሪ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ምን አሉ? በጆ ባይደን እድሜ መግፋት እና በአቅም ማጣት እጩ ፕሬዚደንትነታቸውን ከጥቂት ወራት በፊት የሰጧቸው ካማላ ሐሪስ ትናንት ሽንፈታቸውን በተቀበሉበት ንግግራቸው፦ «አናሸንፍም ማለት አይደለም» ብለዋል ።
ወደፊት ትግላቸውን እንደሚገፉበትም በፈገግታ ተውጠው በወጡበት መድረክ ላይ ገልጠዋል ። ካማላ ሐሪስ የወደፊት የዴሞክራቶች ወኪል ሆነው ሊቀጥሉ እንደሚችሉም ቁምታ ተሰጥቷል ።
ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ቻላል ።
አበበ ፈለቀ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ