የፕሬዝዳንት ፑቲን የሰሜን ኮሪያና ቬትናም ጉብኝት
ሐሙስ፣ ሰኔ 13 2016ዘ ሄግ ነዘርላንድስ በሚገኘው ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት በቀረበባቸው ክስ የእስር ማዘሻ የተቆረጠባቸውና አውሮፓና አሜሪካ ማዕቀብ የጣለባቸው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን በሰሜን ኮሪያና ቪየትናም የላቀ የመሪ ጉብኝት በማድረግ የሁለትዮሽ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። ምራባውያን በዩክሬን ጦርነት ምክንያት እንደወራሪና የጦር ወንጀለኛ የሚቆጥሯቸው ፑቲን፤ በሌላው ዓለም እንዲወገዙና እንዲገለሉ የሚፈለግ ቢሆንም፤ ከዚህ ቀደም በቻይና እንደታየው ሁሉ ስሜን ኮሪያና ቪየትናምም ከደመቀ አቀባበልና መስተንግዶ ባለፈ የወታደርዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮችንም ተፈራርመዋል።
የፕሬዝዳንት ፑቲንና የኪም ዮንግ ወታደራዊ ስምምነት
በኒውክለር ፕሮግራሟ ምክንያት ለዓመታት በዓለም አቀፍ ማዕቀብ ውስጥ ያለችው የስሜን ኮሪያ መሪ ኪም ዮንግ ባሰሙት ንግግር ፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ሉአላዊነቷንና ነጻነቷን ለማስከበር የምታካሂደው ሕግ የማስከበር ዘመቻ መሆኑን በማመልከት ድጋፋቸውን ሲገልጹ፤ ፕሬዝዳንት ፑቲንም፤ ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ጦርነት ላይ ትከተለዋለች ያሉትን ሚዛናዊ ፖሊሲ የሚያደንቁ መሆኑን ገልጸዋል። ሁለቱ መሪዎች ስሜን ኮሪያና ሩሲያ በሁለቱም ይሁን ባንዳቸው ላይ የሚፈጸምን ወታደራዊ ጥቃት በጋራና በአንድነት ለመካላከል የሚያስችል ወታደራዊ ስምምነት መፈራረማቸው ታውቋል። በስምምነቱም፤ ስሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያዎችን ሚሳይሎችንና ተተኳሾችን ለሩሲያ የምታቀርብ ሲሆን፤ ሩሲያ ደግሞ በመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ በመተላለፍ ጭምር ለኒውክለር ፕሮግራሟ ድጋፍ ልታደርግ ትችላለች እየተባለ ነው። ፕሬዝድንት ፑቲን ግን፤ ምራባውያን ዩክሬን በሩሲያ ላይ እንድትጠቀምበት ኤፍ 16 የመሠሉ የጦር አውሮፕላኖችን ጭምር እየሰጡ ባለበት ሁኔታ፤ ሩሲያ ከስሜን ኮሪያ ጋር የምትፈጥረው ወታደራዊ ስምምነት የሚያነጋግር ሊሆን እንደምይገባው ነው የገለጹት።
ስምምነቱ በአካባቢው የሚፈጥረው ተጽኖና አሳሳቢነቱ
ይህ ስምምነትና አቋምም ሩሲያንክስሜን ኮሪያ ጎን በማስለፍ ከደቡብ ኮሪያ ጎን ክቆመችው አሜሪካ ጋር የሚያፋጥጥና በአካባቢውም አዲስ የኃይል አሰላለፍ የሚፈጥር እንዳይሆን ያሰጋል እየተባለ ነው። አሜሪካ ስምምነቱን አሳሳቢ ስትል ማውገዟ ተዘግቧል። የፔንታጎን ቃል አቀባይ ጀነራል ፓትሪክ ሬይደር፤ «የሩሲያና ስሜን ኮሪያ ግንኙነት በዚህ ደረጃ ጥብቅና ጥልቅ መሆኑ በተለይ ለኮሪያ ባሕር ወሽመጥ ሰላም አሳሳቢ ነው» በማለት አሜሪካ ጉዳዩን በቅርብ የምትከታተለው መሆኑን ገልጸዋል።
ቀድሞ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማት የነበሩት ሄንርይ ሃጋርድ በበኩላቸው የፕሬዝዳንት ፑቲን የስሜን ኮሪያ ጉብኘትና ስምምነት፤ በዋናነት ወታደራዊ ስምምነት ቢሆንም ከዚያም በላይ ግን ይላሉ፤ «ከዚያም በላይ ሩሲያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ይህን የመስለ ወታደርዊ ስምምነት በማድረግ የደርሰባትን ዓለም አቀፍ መገለል ተቋማዊ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን፤ በሰሜን ኮሪያ በኩል ግን ስምምነቱ ከመገለል መውጫ መንገድ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ገልጸዋል።
የፕሬዝዳንት ፑቲን የቬትናም ጉብኝትና የአገሪቱ `የባምቦ` ዲፕሎማሲ
የፑቲን የቪትናም ጉብኝት ግን ከስሜን ኮሪያም ይበልጥ ምዕራባውያንን ሳያስከፋ እንዳልቀረ ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት። ቪትናም ምንም እንኳ ከሩሲያ ጋር የቆየና ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላት ቢታወቅም፤ በአሁኑ ወቅት፤ ከአሜሪካና ከምራባውያኑ አገሮች ጋር ከፍተኛ የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር የመሰረተች በመሆኑ በምዕራባውያን እንደ ወንጀለኛ የተፈርጁትን ፕሬዝዳንት ፑቲንን በዚህ መጠን ተቀብላ ታስተናግዳለች ተብሎ ያልተገመተ በሚመሰል ሁኔታ፤ አንዳንዶች ቅሬታ ቁጣቸውን ሲገልጹ ተስምተዋል።
ቬትናም ግን ከሩሲያ ጋር ዘርፈ ብዙና የቆየ የኢኦኖሚ ግንኑነት እንዳላት ነው የሚታወቀው። በተለይም በወታደራዊ ቴክኖሊጂ የሩሲያ ጥገኛ እንደሆነች የሚገለጽ ሲሆን፤ በዚህም ይሁን በሌላ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት በማስቀጠል ብሔራዊ ጥቅሟን እንደምታራምድ ነው የሚገለጸው። በአውስትራሊያ የኒው ዌልስ ዩንቨርስቲ ኤሚሪትስ ፕሮፌሰር ካርልይሌ ታየር እንደሚሉት በተለያዩ ኢኮኖሚያዊና መልክአ ምድራዊ ፖለቲካዊ ምክንያቶች የሩስያ መዳከምና መገለል የቬትናም ፋላጎት አይደለም፤ «ቬትናም ጥቅሟን ለማስክበር ከሁሉም ወገኖች ጋር ግንኑነትን የመፍጠርን ፖሊሲ የምትከተልና የሩሲያ መዳከምና መገለልንም የማተፈልግ ናት» በማለት ሩሲያ በአካባቢውም የኃይል ሚዛን ለማስጠበቅ ተፈላጊ መሆኗንም አውስተዋል። ቬትናም በብሔራዊ ጥቅም ላይ ተመስርቶ ከተለያዩ ተጻራሪ ኃይሎች ጋርም ቢሆን ግንኙነትን የመመስረትና የማራመድን አንድንዶች የባምቦ ዲፕሎማሲ የሚሉትን ፖሊሲ የምትከተል ናት በማለትም በዚህ ምክንያት ቬትናም ከማንኛውም፤ ከሰይጣን ጋርም ቢሆን ከስምምነት ልትደርስ እንደምትችል ፕሮፊሰር ካርልይሌ አስገንዝበዋል።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ