የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ትምህርት
እሑድ፣ ኅዳር 17 2010ማስታወቂያ
በኦሮሚያ እና ሶማሌ አጎራባች ክልሎች የተፈጠረው ለበርካቶች ሞትና በአስር ሺዎች መፈናቀል ምክንያት በሆነው ግጭት እና በሰበቡ እና ካለፉት በተካሄዱተቃውሞ ሰበብ በሁለቱም ክልሎች የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፣ በክልሎቹ በተፈጠረው አለመረጋጋትም ትምህርት በአግባቡ የሚሰጥበት ሂደት እክል እንደገጠመው እና አሁንም ቢሆን ተማሪዎች እንደሚፈለገው ትምህርታቸውን መከታተል እንዳልቻሉ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ተማሪዎች ይናገራሉ። የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ለደህንነታቸው አስጊ ነው በሚል ወደ ዩኒቨርሲቲው መሄድ የለባቸውም በማለት በተለያዩ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ተቃውሞ ማድረጋቸው ይታወሳል።
አርያም ተክሌ
ማንተጋፍቶት ስለሺ