1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባላት ጉዳይ

ሰኞ፣ የካቲት 18 2016

የኢትዮጵያ መንግሥት በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው የፌዴራል፣ የክልሎች እና የከተማ መስተዳድር አምስት የምክር ቤት አባላት መካከል የ ሦስቱ ያለመከሰስ መብት ባለፈው ሳምንት ተነስቷል።

https://p.dw.com/p/4ctw9
ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደኣ
ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደኣምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባላት ጉዳይ

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤት አባላት ጉዳይ

የኢትዮጵያ መንግሥት በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው የፌዴራል፣ የክልሎች እና የከተማ መስተዳድር አምስት የምክር ቤት አባላት መካከል የ ሦስቱ ያለመከሰስ መብት ባለፈው ሳምንት ተነስቷል።የምክር ቤት አባላት ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር ያለመከሰስ መብታቸው በዘፈቀደ እንደማይነሳ በሕግ ቢደነገግም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 3 / 1990 ላይ ያለመከሰስ መብታቸው ሊነሳ የሚችልበት የአሠራር ድንጋጌ መኖሩን አንድ የሕግ ባለሙያ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

የሕግ ባለሙያው አክለው እንዳሉት የምክር ቤት አባላቱ ያለመከሰስ መብት መነሳቱ ካልቀረ እስካሁን በእሥር ላይ ሆነው የተንገላቱበት ሁኔታ ትክክል እንዳልነበር ገልፀዋል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት በቁጥጥር ሥር የዋሉት አምስቱም የምክር ቤት አባላት ጠበቃ የማግኘትም ሆነ ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸው አልተጠበቀላቸውም።የፖለቲከኛ ታዬ ደንደዓ መታሰር

 

የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት አነሳስ

 

የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት
የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ምስል Seyoum Getu/DW

ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በአማራ ክልል የሚፀና ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎች አካባቢዎችም ይተገበራል በተባለው ፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባለፈው ሳምንት ያለመከሰስ መብታቸው ከተገፈፈባቸው ሰዎች መካከል የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሃንስ ቧያለው እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት እባል እና የሰላም ሚኒስትር ድኤታ ጭምር የነበሩት አቶ ታዬ ደንደዓ ይገኙበታል። በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ካሳ ተሻገርም ያለመከሰስ መብታቸው በሳምንቱ መጨረሻ ተነስቷል።የፌደራል እና ክልል ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ 53 ግለሰቦች አዋሽ አርባ መታሰራቸውን ኢሰመኮ አረጋገጠ።

የሕዝብ ተወካዮችም ይሁኑ የክልል ምክር ቤት አባላት ወንጅል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር ይህ መብታቸው በሌላ ሁኔታ የሚነሳበት መንገድ ምን ሊሆን ይችላል ስንል የጠየቅናቸው ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ አካሄዱን "የሥነ ሥርዓት ጉዳይ ነው" በማለት ገልፀውታል። ይህም ማለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 3 /1990 ላይ በወንጀል እጅ ከፍንጅ ያልተያዙ የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብታቸው የሚነሳበት ሥነ ሥርዓት በግልጽ መቀመጡን አብራርተዋል።

 

በርካቶችን ለእሥር የዳረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

 

የኦሮምያ ምክር ቤት
የኦሮምያ ምክር ቤት ምስል Seyoum Getu/DW

ባለፈው ዓመት መጨረሻ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ እንዲሁም ሕግ እና ሥርዓትን ለማስከበር በሚል መደንገጉ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ አምስት የተለያዩ ምክር ቤቶች አባላትን ጨምሮ ጋዜጠኞች ፣የመብት ተሟጋቾች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አዋሽ አርባን ጨምሮ በተለያየ ስፍራ ታሥረዋል።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዶክተር ጫላ ዋታን ያለመከሰስ ልዩ መብት አነሳ

ስድስት ወራት ቆይቶ እንደገና ለአራት ወራት በተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የተያዙ የምክር ቤት አባላት  ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ ፣ ጠበቃ እንዳያገኛቸው እና ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ክልከላ ተደርጎባቸውም ቆይተዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የመብት ድርጅት የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት መንግሥትን የሚተቹ ታዋቂ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ በማሰር ሰላማዊ ተቃውሞን ለማፈን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተጠቅመዋል" ማለቱ ይታወሳል።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ