1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደም ዝዉዉር መታወክ (ስትሮክ)

ማክሰኞ፣ ሰኔ 13 2009

ድንገት የሚከሰት የጤና ችግር ነዉ። አካልን በአንድ ወገን በድን ወይም ሽባ ሊያደርግ ይችላል፤ ሲከፋም ሕይወትን ይቀጥፋል። በህክምናዉ ስትሮክ በመባል ይታወቃል፤ ብዙዎችም እንዲሁ ስትሮክ ሲሉት ይደመጣል። ይህን የጤና እክል የዘርፉ የህክምና ባለሙያ የሆኑት ኢትዮጵያዊ በአንጎል ዉስጥ የደም ዝዉዉር መታወክ ሲሉ ይገልጹታል።

https://p.dw.com/p/2f3eF
Schlaganfall Symbolbild
ምስል Sebastian Kaulitzki - Fotolia.com

ደም ዝዉዉር መታወክ (ስትሮክ)

 የደም ዝዉዉር መታወክ ማለትም ስትሮክ አካል እንዳይታዘዝ ከማድረግ አልፎ አዕልሮ ላይ ተያያዥ ችግሮችን ማስከተል እንደሚችል አንዳንድ ታማሚ ሰዎችን ማስተዋሉ በቂ ነዉ። ይህ ለሽባነት ብሎም ለህልፈተ ሕይወት የሚያበቃ ስትሮክ የተባለ የጤና ችግር በትክክል ምንድነዉ? ለዚህስ የሚያጋልጠዉ መንስኤ? መከላከልስ የሚቻልበት መንገድስ አለ? ዶክተር ተስፋዬ በርኼ በቅዱስ ጳዉሎስ ሚሊኒየም ሆስፒታል የህክምና ኮሌጅ የዉስጥ ሕክምና ዘርፍ የነርቭ ክፍል የነርቭ ሃኪም እና መምህር ናቸዉ። የደም ዝዉዉር መታወክ ከደም ግፊት፤ ከልብ ሕመም ከደም ዉስጥ ስብ ወይም ኮሌስትሮል እንዲሁም ከስኳር ጋር የተያያዘ የጤና እክል ካለ፤ በቂ የሰዉነት እንቅስቃሴ የማናደርግ ከሆነ፤ ትምባሆ ማጨስ እንዲሁም አልክሆል መጠጥ ማብዛት ከታከሉበት የመከሰቱን አጋጣሚ እንደሚያባብሰዉ ያስረዳሉ። አንድ ሰዉ ለዚህ ችግር ሊያጋልጡ የሚችሉት እነዚህ መንስኤዎች አስቀድመዉ እንዳሉ ካወቀ ያላሰለሰ ክትትል ማድረግ እንደሚኖርበትም ይመክራሉ። እናም አመጋገብ ማስተካከልን ጨምሪ አካላዊ እንቅስቃሴን የሕይወታችን አንድ አካል ማድረግ እንደሚያስፈልግም ያሳስባሉ። አስቀድሞ የሚደረገዉ ጥንቃቄ ችግሩ ድንገት የሚከሰት እንደመሆኑ ማስቀረት ቢያቅት እንኳ የጉዳቱን መጠን መቀነስ ይቻል ይሆናል ተብሎም ይታመናል። በአሁኑ ጊዜም ይህ የጤና ችግር ኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙዎችን እያጠቃ እንደሚገኝም አመልክተዋል።ሙሉ ቅንብሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

Symbolbild Herz Herzerkrankung Herzanfall Herzattacke
ምስል Imago/Science Photo Library

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ