ደን ሕይወት ነዉ
እሑድ፣ ሚያዝያ 19 2006ማስታወቂያ
ደን ሕወት ነዉ የሚባለዉም ያለምክንያት አይደለም። በሚገኝበት ስፍራ ለአካባቢ ተፈጥሮዉ፤ ለአየር ጠባዩ ሚዛን፣ ለአካባቢዉ ማኅበረሰብ ና ዕለታዊ ኑሮም ሆነ በሀገርም ደረጃ የሚሰጠዉ ኤኮኖሚያዊ ጥቅም በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ኢትዮጵያ ዉስጥ በአንድ ወቅት እጅግ መመናመኑ የዘርፉን ምሁራን ብቻ ሳይሆን ብዙዎችን ሲያሳብ እና ሲያነጋግር ቆይቷል ዛሬም እያነጋገረ ነዉ። በአንፃሩ ደንን ለማልማት በመንግስታዊ መሥሪያ ቤቶችም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሳይቀር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተጀመረዉ ጥረት አበረታች ነዉ። ዶቼ ቬለ በኢትዮጵያ የደን ይዞታና ደንን ለማበልጸግ የሚደረጉ ሥራዎች ላይ ዉይይት አካሂዷል።
ሙሉዉን ዉይይት ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ፤
ሸዋዬ ለገሠ
ልደት አበበ