1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ገንዘብ ወይስ ጥረት?

ዓርብ፣ ጥቅምት 30 2016

ወጣቶች በታዳጊነት ዘመናቸው የተለያዩ የህይወት ምዕራፎች ውስጥ ያልፋሉ። እያንዳንዱ ወጣት ግን የህይወት ምዕራፉን ፈተና በእኩል ጥረት፤ በእኩልም ብርታት ያልፋል ማለትም አይደለም፡፡ለመሆኑ በታዳጊዎች አስተዳደግ ውስጥ የቤተሰብ የገቢ ሁኔታ እንዴት ያለ ሚና ይኖረው ይሆን የሚለው ዛሬ ታዳጊዎች ሁለት ጎራ ይዘው የሚሞግቱበት ነው፡፡

https://p.dw.com/p/4Ybt8
Äthiopien Addis | GOM Reporterin Sumeya Samuel & ihre "Money or Effort" Geste
ምስል S. Getu/DW

ገንዘብ ወይስ ጥረት?

ከገንዝብ ይልቅ ጥረት

የግል ጥረት ለስኬታማ ህይወት ዋነኛውን ሚና ይጫወታል በሚል አራት ታዳጊዎች ያምናሉ። ሶስቱ ሴት ታዳጊዎች ሲሆኑ አንደኛው ወንድ ታዳጊ ነው፡፡ ታዳጊዎቹ ሃሳባቸውን ሲያስቀምጡ ከገንዝብ ይልቅ ጥረትን ማውረስ ይገባል ይላሉ።  ጥረት የገንዘብ ማግኛ ስልትንም ስለሚቀይስ ነው ባይ ናቸው፡፡ በዚህ ሃሳብ የሚሞግቱ ታዳጊዎች በገንዘብ አቅም ልጆችን የሚያሳድጉ ወላጆች ለልጆቻቸው ቀርበው ጥረት የማስተማር እድላቸው አነስተኛ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡ ታዳጊዎቹ በአስተያየታቸው ያለ በቂ ጥረት የሚገኝ ገንዘብ ፈታኙን የህይወት ምእራፍ ስለማያሳይ ገንዘብ ያመጣው ስኬት እርካታ የማያስገኝ እና ወደ ደስታ ጥግም የማያሻግር ነው ሲሉ ይሞግታሉ፡፡

«ገንዘብ ስኬትን ለማውረስ ቁልፉን ሚና ይጫወታል»ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የወጣቶችና የወላጆች ግንኙነት

ገንዘብ ለስኬት ቁልፉን ሚና ይጫወታል በሚል ሃሳብ ለመሞገት የቀረቡት ደግሞ ሁለት ሴቶች እና አንድ ወንድ ታዳጊዎች ናቸው፡፡ በዚህ ጎራ የተቀመጡ ታዳጊዎች ገንዘብ ስኬትን ለማውረስ ቁልፉን ሚና ይጫወታል ሲሉ የራሳቸውን ምክኒያታዊ ሃሳብ በማስቀመጥ ነው፡፡ ነገሮችን የሚያቀለው ገንዝብ በጥረት ሊባክን የሚችለውን ጊዜ ከመቆጠቡም በላይ ለስኬታማነት የሚከፈልን መስዋዕትነት ያቀላል ይላሉ፡፡ በዚህም በበቂ ገንዘብ የታገዘ የአስተዳደግ ስልት የተመጣጠነን ምግብ ከማግኘት ጀምሮ በቂ ህክምና ብሎም በገንዝብ የሚቀለውን የመኖሪያ ቁሳቁስ ስለሚያስገኝ ለስኬት የመቅረብ እድሉ ሰፊ ነው ባይም ናቸው፡፡ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የሱስ ተጋላጭ የነበረችው ወጣት

ታዳጊዎቹ ከ12-18 ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አምስት ሴት ታዳጊዎች እና ሁለት ወንድ ታዳጊዎች ለክርክሩ ተቀምጠዋል፡፡


አወያይ፡ ሱመያ ሳሙኤል

አዘጋጅ፡ ሥዩም ጌቱ