1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በደረሰው ጥቃት 16 ሰዎች ተገደሉ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 12 2015

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ምግር በሚባል ስራ ሰሞኑንን በተደጋጋሚ በደረሰው ጥቃት ከ16 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናገሩ፡፡ ነዋሪዎቹ ጥቃቱ ከትናንት በስትያ ሐሙስ መድረሱን ገልጸው ለጥቃቱ ሸኔን እናጠፋን በማለት በስፍራው በፋኖ ስም ይንቀሳቀሳሉ ያሉትን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/4IYDh
IDPs from Horo guduru wollega
ምስል Seyoum Getu/DW

በሆሮ ጉዱuru ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሰዎች ተገደሉ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ምግር በሚባል ስራ  ሰሞኑንን በተደጋጋሚ በደረሰው በደረሰው ጥቃት ከ16 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናገሩ፡፡ ነዋሪዎቹ ጥቃቱ ከትናንት በስትያ ሐሙስ መድረሱን ገልጸው ለጥቃቱ ሸኔን እናጠፋን በማለት በስፍራው በፋኖ ስም ይንቀሳቀሳሉ ያሉትን ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ አድርገዋል።  በወረዳው ጃቦ ዶቤን በሚባል ስፍራ ደግሞ የሼነ ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ሲያደርሱ እንደነበር የቀበሌው ነዋሪዎች ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ በአሙሩ ወረዳ የደረሰውን የታጣቂዎች ጥቃት አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከወረዳ እስከ ዞኑ ዋና አስተዳደሪ እና ከክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ ጋር ስልክ ቢደውልም ፈቀደኛ ባለመሆናቸው አልተሳካም፡፡ጥቃት ግድያ በሆሮጉዱሩ ወለጋ አሙሩና ጃርደጋ ጃርቴ አከባቢዎች

ሰሞኑን የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ጥቃት ማድረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ በወረዳው ምግር በተባለ አካባቢ ከትናንት በስቲያ በደረሰው ጥቃት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉንና የተፈናቀሉ ዜጎችም አጋምሳ ወደ ተባለ ከተማ ሸሽተው እንደሚገኙም ጠቁሟል፡፡ በሰሞኑ ጥቃት ከአስር በላይ ሰዎች በአንድ ቦታ ህይወታቸው ማለፉንም ገልጸዋል፡፡በምዕራብ ኦሮሚያ የፀጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የነዋሪዎች እንግልት

በአሙሩ ወረዳ ምግር ቀበሌ በዚህን ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት መድረሱን ሌላው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ ሐሙስ በደረሰው ጥቃት ህይወታቸው ያለው  በብዛት ሴቶች ሲሆኑ፣ ህጻናትና ሽማግሌዎችም እንደሚገኙበት አክለዋል፡፡

 " በብዛት የሞቱት ሴቶች ናቸው፡፡ 12 ሴቶች ህይወታቸው አልፏል፡፡ 3 ወንዶች መሞታቸው ተረጋግጠዋል፡፡ ነዋሪው እስካሁን የተጎዱትን በየጫካው እየፈለገ ይገኛል፡፡ ጆጂና ምግር የሚባሉ ቦታዎች ከአጋምሳ ከተማ 10 ኪ.ሜት  ያህል ርቀት የላቸውም፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ላይ የወደመውን ቤትና ንብረት ይሄን ያህል ነው ብሎ መገመትም የዳግታል ብሏል፡፡ "

በወረዳው በተለይም ከባለፈው ሳምንት እሁድ አንስቶ አምስት በሚደርሱ ቀበሌዎች ውስጥ ጥቃቶች መድረሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ወደ አጋምሳ ከተማ ተፈናቅለው የሚገኙት ሌላው ነዋሪም በተመሳሳይ ምግርና ጆጅ በሚባል አካባቢ በደረሰው ጥቃት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተናግረዋል፡፡የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ተፈናቃዮች አቤቱታ

በጉዳዩ ላይ ከወረዳው አስተዳደርና ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምረሳ ፌጤ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስልካቸውን በተደጋጋሚ ባለማንሳታቸው አልተሳካም፡፡ የክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በጉዳዩ ላይ በስልክ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ለማካተት አልተቻለም፡፡  በአሙሩ ምግር በተባለ ቦታ ላይ ባለፈው እሁድም በተመሳሳይ በደረሰው ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በአካባቢ በተለያዩ ጊዜ ታጣቂዎች በንጹህ ዜጎችና ንብረት ላይ ጉዳት እያደረሱ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶቸ ጉባኤ ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ