1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን አስመራ ገባ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 11 2010

465 መንገደኞች የጫነዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመርያ በረራዉን ወደ አስመራ ዛሬ ጀመረ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ በዕለቱ ወደ ኤርትራ መዲና አስመራ በረራ ይኖረዋል።

https://p.dw.com/p/31e9K
Äthiopien Rückkehrer am Flughafen Asmara
ምስል Ethiopian Broadcasting Corporation
Äthiopien Addis Abeba Ethiopian Airlines neuer Linienflug nach Eritrea
ምስል Getty Images/AFP/H. Tadese

456 መንገደኞች የጫነዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመርያ በረራዉን ወደ አስመራ ዛሬ ጀመረ። የተለያዩ የኅብረተሰብ አካላችን ተቀማጭነታቸዉ አዲስ አበባ የሆኑ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶችን ፤ ወደ 20 ዓመታት የተነጣጠሉ ቤተሰቦችን እንዲሁም ጋዜጠኞችን ያሳፈረዉ 787 ቦይንግ ጀት ከአንድ ሰዓት ተኩል በረራ በኋላ አስመራ ገብቶአል። በዚሁ በረራ ላይ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደስ አለኝ እና ባለቤታቸዉ ወይዘሮ ሮማንም ይገኛሉ። አቶ ኃይለማርያም ደስ አለኝ ወደ ኤርትራ የሚጓዘዉን የመጀመርያ በረራ በመምራት ወደ አስመራ እንደተጓዙ የሃገር ዉስጥ መገናኝ ብዙሃን ዘግበዋል።

አዜብ ታደሰ