በሃድያ ዞን ሰዎች በኩፍኝ በሽታ እየሞቱ ነው
ሐሙስ፣ ጥር 30 2016በሃድያ ዞን ሰዎች በኩፍኝ በሽታ እየሞቱ ነው
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሃድያ ዞን ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ ለገኖ ቀበሌ ጎጥ 06 የምትባለው መንደር ሳምንቱን የሀዘን ድባብ እንዳጠላባት ነው የሰነበተችው ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የጎጥ 06 መንደር ባለፉት ሦስት ሳምንታት ብቻ የአምስት ህጻናትን ሞት አስተናግዳለች ፡፡ የመንደሩ ነዋሪ የሆኑት አቶ ደርቤ ማዴቦ የስድስት ዓመት ልጃቸውና አንድ ሌላ የጎረቤት ልጅ በኩፍኝ በሽታ ከተያዙ በኋላ ህይወታቸው ማለፉን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ፡፡
“ ልጄን ሀይለኛ ትኩሳት ሲይዘው ሾኔ ሆስፒታል ወስጄው በሽታው ኩፍኝ መሆኑን ሀኪሞቹ ነገሩኝ “ የሚሉት አቶ ደርቤ “ ህክምና እየተደረገለት እያለ ከሳምንት በኋላ ባለፈው አሁድ ሕይወቱ አልፎ ሰኞ ዕለት ቀብሩን ፈጽመናል ፡፡ የጎረቤቴ የአቶ ተረፈ ላጲሶ ልጅም ከሦስት ሳምንት በፊት እንዲሁ መጀመሪያ ታመመ ፡፡ ከዛም አንጀቱ ቆስሏል ተብሎ ሁለት ቀን ከቆየ በኋላ ሞቶ ቀብረነዋል” ብለዋል ፡፡ አዲስ አበባ፤ የኩፍኝ በሽታ ምልክት በሁሉም ክልል ከተሞች መታየቱ
በሃድያ ዞን በምስራቅ ባድዋቾ ወረዳ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ የአቶ ደርቤን እና ጎረቤታቸውን ጨምሮ የአካባቢው ህጻናትን ለሞት እየዳረገ ይገኛል ፡፡ የወረዳው ነዋሪዎች እንዳሉት የኩፍኝ በሽታው በአካባቢው መታየት የጀመረው በታህሳስ ወር ውስጥ ነው፡፡ ህጻናቱን ለሞት መዳረግ የጀመረው ግን ካለፉት ሦስት ሳምንታት ወዲህ ነው ፡፡
የፈውስ ህክምና
በሃድያ ዞን ምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ እየተሰፋፋ ይገኛል በተባለው የኩፍኝ በሽታ ዙሪያ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሃድያ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ ታከለ ኦልበሞ በሽታው መከሰቱንና ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠዋል ፡፡ እስከአሁን ስምንት ሰዎች በበሽታው ህይታቸው ማለፉን ከጤና ተቋማት ደርሶኛል ያሉት ሪፖርት የጠቀሱት አቶ ታከለ “ በሽታው ተላላፊ በመሆን በህመም ላይ ያሉትን ከሌሎች በሽተኞች በበአማራ ክልል በኩፍኝ ወረርሽኝ 46 ሰዎች ሞተዋልመለየት ህክምና እየተሠጠ ይገኛል ፡፡ እስከአሁን 180 ህጻናት ህክምና ተሰጥቷቸው ወደ ቤታቸው ሄደዋል ፡፡ አሁንም በህክምና ላይ የሚገኙ አሉ “ ብለዋል ፡፡ በአማራ ክልል በኩፍኝ ወረርሽኝ 46 ሰዎች ሞተዋል
የዞኑ ጤና መምሪያ ሃላፊ እስከአሁን በበሽታው የሞቱት ስምንት ናቸው ቢሉም አንዳንዶች ወደ ህክምና ተቋማት ያልመጡትን ጨምሮ ቁጥራቸው ከዚህ ሊበልጥ ይችላል እያሉ ነው ፡፡ አንድ የሾኔ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ብቻ ታመው ወደ ሆስፒታሉ ከመጡት መካከል 22 ሰዎች መሞታቸውን እንደሚያውቁ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል ፡፡ አሁን ላይ በቀን እስከ አሥር የሚደርሱ የኩፍኝ በሽታ ተጠቂዎች በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታሉ እየገቡ እንደሚገኙ የተናገሩት የህክምና ባለሙያው “ የመኝታ ጥበት በማጋጠሙ አማራጭ ድንኳኖችን በማዘጋጀት የህክምና ድጋፍ እያደርግን እንገኛለን “ ብለዋል፡፡ የኩፍኝ ወረርሺኝ በኮንጎ ሺህዎችን እየቀጠፈ ነው
የመከላከል ሥራው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ከቀናት በፊት በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ በበሽታው ዙሪያ የጋራ ምክክር አካሂደዋል ፡፡ በምክክሩ ላይ ኩፍኝን ጨምሮ ወረርሽኞችን ፈጥኖ ያለመለየትና ፈጣን ምላሽ ያለመስጠት፣ ቅንጅታዊ አሠራሮችን ያለማጠናከር፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ትኩረት ማነስ ፣ የሰው ሀይል አለመሟላት እና የበጀት እጥረት ለበሽታው መከሰት ምክንያት መሆናቸው በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡ በአሁኑ ወቅት በበሽታው ለተያዙት ህክምና ጎን ለጎን በሽታው እንዳይስፋፋ ለማድረግ የቫይታሚን ኤ ዕደላን እና ክትባትን ጨምሮ የተለያዩ ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኝ የሃድያ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊው አቶ ታከለ ጠቅሰዋል ፡፡
ምስል ከክልሉ ጤና ቢሮ የተወሰደ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ