1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«በርሊናለ» የፊልም ፊስቲቫልና የአፍሪቃዉያን ተሳትፎ

ሐሙስ፣ የካቲት 22 2010

የኛን ፊልም የሚከታተሉ በአፍሪቃ አህጉር የሚኖሩ ተተከታታዮች ከጊዜ ወደጊዜ ፊልሞቻችን ለመመልከት ፍላጎታቸዉ እየጨመረ ነዉ። እነዚህ የፊልም አፍቃሪዎች ለረጅም ዘመናት አትኩሮታቸዉ የነበረዉ ግን የአሜሪካንን ፊልምና የአሜሪካን ታሪክ የሚተርክ ፊልምን መከታተል ላይ ብቻ ነበር።

https://p.dw.com/p/2tXq9
Pressekonferenz zur 68. Berlinale
ምስል picture-alliance/dpa/B. Pedersen

የጀርመን የፊልም ፌስቲቫል «በርሊናለ» እና ኢትዮጵያውያን

 

ዘንድሮ ለ 68ኛ ጊዜ የተካሄደዉ የጀርመኑ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ “በርሊናለ” ባለፈዉ ሳምንት መጠናቀቅያ እሁድ አብቅቶአል። ለአስር ቀናት የተካሄደዉ ይኸዉ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ "Touch me not" የተሰኘዉ እና በአንዲት ሩሜኒያዊት የፊልም ሥራ ባለሞያ የቀረበዉ ፊልም ስለሰዎች ወሲባዊ ስሜታዊ መንፈሳዊ አካላዊ ግንኙነት አገላለፅ ላይ የሚያዉጠነጥ ነዉ። ፊልም  የጀርመኑን ዓለማቀፍ የፊልም ፊስቲቫል የወርቅን ወስዶአል። ዘንድሮ በአሸናፊነት የወጣዉ ይኸዉ የሩሜኒያዉ ፊልም ብዙ አድናቂ ሳይኖረዉ መዉጣቱ የዚሁ መድረክ አዘጋጅ የጀርመን ፊልም ያለምንም ሽልማት ባዶጁን መዉጣቱ ብዙ አነጋጋሪ ሆንዋል በዚህ  ዝግጅታችን ለአስር ቀናት የዘለቀዉን አለም አቀፉን የጀርመን ፊልም ፊስቲቫል እንመለከታልን።

68. Berlinale | Preisträger Adina Pintilie - Goldener Bär für den Besten Film
ምስል Getty Images/T. Niedermueller

ባለፈዉ ሰሞን የተጠናቀቀዉ እና ለአስር ዘናት የዘለቀዉ በርሊን ላይ የሚዘጋጀዉ የጀርመኑ ዓለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫል በርሊናል በመድረኩ ከዓለም ሃገራት የተሰባሰቡ ከአራት መቶ በላይ ፊልሞች የተስተናገዱበት እንደሆነ ታዉቋል። ለዉድድር ከቀረቡት 19 ፊልሞች መካከል ምርጥ ፊልም ሆኖ ተመርጦ ወርቅማዉን ድብ ሽልማት ያገኘዉ በሩሜንያዊትዋ የፊልም ስራ አዋቂ በ Adina Pintilie የተሰራዉ "Touch me not" የተሰኘዉ ፊልም ነዉ። የብር ሽልማቱን ደግሞ የፖላንዱ « Twarz» ማለትም እቃ የተሰኘዉ ፊልም ነዉ። ፊልሙ ከገጠር ወደ ሰፊ ከተማ ሄዶ በስራ ላይ የነበረ ሰዉ በስራ ላይ በደረሰበት አደጋ ስራዉን በቀጣይ መስራት አቅቶት ወደነበረበት ገጠር የተመለሰን ሰዉ ታሪክ የሚያሳየዉ ፊልም መሆኑም ተዘግቦአል። አወዛጋቢ የሆነዉና የበርሊናለን ከፍተኛ ሽልማት ማለትም የወርቁን ድብ የወሰደዉ በሩሜንያዊት የፊልም ሥራ ባለሞያ የተሰራዉ ፊልም ስለሰዎች የወሲብ  ስሜት መንፈሳዊ አካላዊ ግንኙነት አገላለፅ ላይ የሚያዉጠነጥነዉ ፊልም ነዉ። መዲና በርሊን ላይ ወደ 4 አስርተ ዓመታት የኖረዉ ባልደረባዬ ይልማ ኃይለሚካኤል የበርሊኑን የፊልም ፊስቲቫል በየዓመቱ ለዘመናት ተከታትሎአል። ዘንድሮ ያልተጠበቀ ፊልም የበርሊናለን የወርቅ ድብመዉሰዱ አስገራሚ አይደለም በርሊን የነፃዉ ዓለም መስኮት መሆንዋ የታወቀ ነዉ ሲል ተናግሮአል።

Berlinale Wettbewerb 2018 Touch Me Not
ምስል Manekino Film, Rohfilm, Pink, Agitprop, Les Films de l'Etranger

በየዓመቱ በሚካሄደዉ በበርሊኑ ዓለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫል ላይ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የአፍሪቃ የፊልም ሥራ ባለሞያዎችን "Berlinale Africa Hub" በሚለዉ ጥላ ሥር ያሰባሰቡት የዓለም ሲኒማ ፕሮጀክት ተጠሪ ቪዚንዞ ቡግኖ እንደገለፁት አፍሪቃዊ የሚባል ፊልም መጠርያ የለም። 

« የአፍሪቃ ፊልም ሲባል መጠርያዉ ትክክለኛ ትርጉሙን አይሰጥም። ምክንያቱም አፍሪቃ እጅግ ሰፊ አህጉር በመሆኑና፤ ከቦታ ቦታ ከሃገር ሃገር የሚሰራዉ ፊልም የተለያየ ይዘትና አስተሳሰብን ስለሚንፀባርቅ ነዉ። እንደ እኔ እምነት በተለያዩ አፍሪቃ ሃገራት በፊልም ሥራ ረገድ  ባለፉት ዓመታት አንዳንድ ነገሮች ላይ ለዉጥ ታይቶአል። በፊልሙ ሥራ ረገድ በእድገትና በሥልጣኔ ደረጃ ካወራን ደቡብ አፍሪቃን ልንጠቅስ ግድ ይላል። በደቡብ አፍሪቃ በፊልም ሥራዉ ረገድ ትልቅ ባህል የሚንፀባረቅበት፤ ከፍተኛ የሞያ ልምድ ያላቸዉ የፊልም ሰራተኞች እና የፊልም ሥራ ሥልጠና የሚሰጥበት ተቋም የሚገኝበት ነዉ።»     

Berlinale 2018 - Berlinale Africa Hub
ምስል DW/A. Steffes-Halmer

ለምሳሌ በዴሞክራቲክ ኮንጎ ዉስጥ በ 1970ዎቹ በቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ማፑቶ ሴሴኮ አመራር ስር በሃገሪቱ ፊልም ቤቶች ሁሉ ለሌላ አገልግሎት ተሸጠዉ ነበር። አሁን አሁን በሃገሪቱ የፊልም ቤቶች ዳግም ብቅ ብቅ እያሉ ነዉ። በጎርጎረሳዊዉ  2014 ዓ,ም በኪንሻሳ ዓለም አቀፍ የፊልm ፊስቲቫል ለመጀመርያ ጊዜ ተካሂዶም ነበር።  በበርሊኑ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ላይ ተካፋይ የነበረችዉ ደቡብ አፍሪቃዊትዋ የፊልም ስራ ባለሞያ ሳራ ቺታምቦ እንደምትለዉ ከሆነ በፊልሙ መድረክ አፍሪቃዉያን  የአፍሪቃዉያን ታሪክን መከታተልን ይሻሉ።  

የኛን ፊልም የሚከታተሉ በአፍሪቃ አህጉር የሚኖሩ ተተከታታዮች ከጊዜ ወደጊዜ ፊልሞቻችን ለመመልከት ፍላጎታቸዉ እየጨመረ ነዉ። እነዚህ የፊልም አፍቃሪዎች ለረጅም ዘመናት አትኩሮታቸዉ የነበረዉ ግን የአሜሪካንን ፊልምና የአሜሪካን ታሪክ የሚተርክ ፊልምን መከታተል ላይ ብቻ ነበር። አሁን ግን የፊልም ተከታታዮች በፊልም ቤት ገብተዉ መመልከት የሚፈልጉት በአፍሪቃዉያን የተሰራ አፍሪቃ ነክ ታሪኮችን የሚያሳዩ ፊልሞችን ነዉ።  ይህ የተመልካች ፍላጎት ደግሞ የምንሰራዉን የፊልም አይነት እና ጥራት እየተሻሻለና እየተቀየር እንዲመጣ አድርጎታል። አፍሪቃ ነክ ታሪክን የሚተርኩ ፊልሞችን የሚመለከት ሰዉ ቁጥር እጅግ  በመጨመሩ በትክክል ጥናት ሳይደረግባቸዉ ቶሎ ቶሎ የሚሰሩ ፊልሞች ተቀባይነታቸዉ ወድቆአል። በፊልም የምንተርከዉ ታሪክ የተመልካችን ቀልብ የሚስብ ሰዎች በታሪኩ ራሳቸዉን የሚያገኙበት ልብን የሚኮረኩር መሆን ይኖርበታል»   

ታዋቂዉ የሆሊዉድ ፊልም ስራ ባለሞያ  Harvey Weinstein ሴትን ተዳፍርሃል በሚል የቀረበበት ከፍተኛ ተቃዉሞ የበርሊኑንም የፊልም መድረክ ጎብኝዎችና የፊልም ስራ አዋቂዎች ያሳተፈ ይመስላል። በዚሁ መድረክ ላይ ሚቱ በሚል አንዳንድ ወንድ የፊልም ስራ ባለሞያዎች የፊልም ተዋናይቶችን ለፆታ ግንኙነት መተንኮሳቸዉን በመቃወም ጥቁር ልብስ የለበሱ ተሳታፊዎች «ሚ ቱ» በሚል መርህ መድረክ ላይ መታየታቸዉን ይልማ ኃይለሚካኤል ዘርዝሮ ገልፆአል።

DW Interview Berlinale 2018 - südafrikanischen Filmemacherin Sara Chitambo
ምስል DW/A. Steffes-Halmer

በየዓመቱ የሚካሄደዉ የበርሊኑ ዓለማቀፍ የፊልም ፊስቲቫል በጎርጎረሳዊዉ 1951 በርሊን ከተማ ላይ የጀመረ ሲሆን በተለይ የበርሊኑ ይህ ዓለም አቀፍ ፊስቲቫል ከሌሎች ለየት የሚያደርገዉ የከተማዋ ፊልም ቤቶች ከዓለም ዙርያ የተሰበሰቡ የተለያዩ አይነት ፊልሞችን ለተመልካች በማቅረባቸዉ እንዲሁም በአስር ቀናቱ የፊልም ፊስቲባል ወቅት ከተማዋ በርካታ ቱሪስቶችን በማስተናገድዋ ነዉ። እምብዛም ተመልካችን ልብ ያልሳበዉ  የዘንድሮዉ የበርሊኑ ዓለም አቀፍ የፊልም መድረክ ሌሎች ጉዳዮችንም ማንሳቱን ይልማ ኃይለሚካኤል እንዲህ ተናግሮአል።ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመቻ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ