1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ውዝግቦችኢትዮጵያ

በአማራ ክልል የደጋ ዳሞት ወረዳ 37 አመራሮች መገደላቸው ተገለፀ

ዓለምነው መኮንን
ቅዳሜ፣ ኅዳር 28 2017

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ 37 የወረዳው አመራሮች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአማራ ክልል መንግሥት ለአመራሮቹ ግድያ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የፋኖ ታጣቂ ተጠያቂ አድርጓል። የመንግሥት ኃይሎች በድሮን ጥቃት መፈፀማቸውን ነዋሪዎች አመልክተዋል።

https://p.dw.com/p/4ns4L
የአማራ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳልኝ ጣሰው
የአማራ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳልኝ ጣሰው “የህዝብና የመንግሥት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ” ያሏቸውንና ታጣቂዎቹ አስረው ካቆዩአቸው 97 ያክል የወረዳው አመራሮች መካከል 37ቱን እንደገደሏቸው ተናግረዋል።ምስል Alemenw Mekonnen/DW

በአማራ ክልል የደጋ ዳሞት ወረዳ 37 አመራሮች መገደላቸው ተገለፀ

ጦርነቱ በአማራ ክልል ከተጀመረ ወዲህ በተደጋጋሚ ጦርነት ካስተናግዱ አካባቢዎች መካከል የፈረስ ቤት ከተማ አንዷ ናት። ከተማዋ ከመስከረም 2017 መጨረሻ ዓም ጀምሮ በፋኖ ታጣቂዎች እንደቆየች ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ደግሞ በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መካክል ወጊያ ሲካሂድ ሰንብቷል። አንድ የዓይን እማኝ በፈረስ ቤትና በአካባቢው ከሀሙስ እለት ጀምሮ በፋኖና መከላከያ መካከል ውጊያው ከበድ ብሎ ሲካሄድ ሰንብቷል ነው ያሉት።

በምዕራብ ጎጃም ዞን የቀጠለው ውግያ

“ድኩል ቃና” በተባለ አካባቢ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከፋኖ ታጣቂዎችና ከንፁሐን 9 ያክል የቆሰሉ ሲሆን 5 ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

37 የደጋዳሞት ወረዳ አመራሮች ስለመገደላቸው

የድሮን ጥቃቱ ሐሙስ እለት የጠነከረ እንደነበር የገለፁልን እኚህ አስተያየት ሰጪ፣ ትናንት ታዲያ የፋኖ ታጣቂዎች ከተማውን ሲለቅቁ ቀደም ሲል በፋኖ ቁጥጥር ስር ከነበሩት 70 ያክል የወረዳው አመራሮች መካከል 37ቱ መገደላቸውን የዓይን እማኙ አመልክተዋል፣ በአካል 37 አስከሬን መቁጠራቸውንና ወደየቤተሰብ እንዲላክ በማድረግ ሥርዓተ ቀብራቸው እንዲፈፀም ማድረጋቸውን ገልጠዋል።

የቱርክ ተዋጊ ድሮን
የዓይን እማኝ የድሮን ጥቃት ባለፈው ሐሙስ ክ4 በላይ ቦታዎች ላይ መጣሉን ገልጠዋልምስል Getty Images/AFP/B. Bebek

በድሮን ጥቃት ሠዎች መቁሰላቸውና መገደላቸው

ሌላ የዓይን እማኝ በበኩላቸው የድሮን ጥቃት ባለፈው ሐሙስ ክ4 በላይ ቦታዎች ላይ መጣሉን ገልጠዋል፣ በተለይ በአንድ መኪና ላይ በደረስ የድሮን ጥቃት ብዙዎች ሳይጎዱ እንዳልቀሩ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ትምሕርት ቤቶች በመዘጋታቸው ሴት ተማሪዎች በግዳጅ እየተዳሩ ነው

በፋኖ ቁጥጥር ስር ከነበሩ የወረዳው አመራሮች መካከልም ከ35 በላይ የሚሆኑት መገደላቸውን መስማታቸውን ተናግረዋል፣ ማን እንደገደላቸውና ስለአገዳደላቸው ግነ እንደማያወቁ አመልክተዋል።

ደመወዝ ያልተከፈላቸው የአማራ ክልል ሠራተኞች አቤቱታ

የከተማው ነዋሪ የነበሩት ቀብር በተለያዩ አብያተክርስቲያናት መከናወኑን ጠቁመው የሌሎች አስከሬንም ወደየትውልድ ቦታቸው መላኩን በስልክ ነግረውናል።

የክልሉ መንግሥት መግለጫ

የአማራ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳልኝ ጣሰው ትናንት ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሰጡት መግለጫ “የህዝብና የመንግሥት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ” ያሏቸውንና ታጣቂዎቹ አስረው ካቆዩአቸው 97 ያክል የወረዳው አመራሮች መካከል 37ቱን እንደገደሏቸው ተናግረዋል። በግድያው የአማራ ክልል መንግሥት ማዘኑንም በመግለጫው ተመልክቷል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከፋኖ ታጣቂዎች በኩል ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት ያደረነው ጥረት አልተሳካም።

ዓለምነው መኮንን

እሸቴ በቀለ