1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ፤ የ HIV ቫይረስ ስርጭት በእጥፍ ጨምሯል ተባለ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሰኞ፣ ኅዳር 30 2017

በትግራይ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መጠን ከጦርነቱ በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ መጨመሩ ተገለፀ። የትግራይ ጤና ቢሮ እንደሚለው በክልሉ የቫይረሱ ስርጭት ከአንድ ነጥብ አራት ከመቶ ወደ ሦስት ከመቶ ጨምሯል። በትግራይ ከተሞች እና የተፈናቃይ መጠልያ ጣብያዎች የኤችአይቪ ስርጭት በስፋት የሚታይባቸው ናቸው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4nuw3
መቀሌ ፤ ትግራይ
መቀሌ ፤ ትግራይ ምስል Million H. Selasse/DW

ትግራይ፤ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት በእጥፍ ጨምሯል ተባለ

ትግራይ፤ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት በእጥፍ ጨምሯል ተባለ 

በትግራይ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት መጠን ከጦርነቱ በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ መጨመሩ ተገለፀ። የትግራይ ጤና ቢሮ እንደሚለው በክልሉ የቫይረሱ ስርጭት ከአንድ ነጥብ አራት ከመቶ ወደ ሦስት ከመቶ ጨምሯል። በትግራይ ከተሞች እና የተፈናቃይ መጠልያ ጣብያዎች የኤችአይቪ ስርጭት በስፋት የሚታይባቸው ናቸው ተብሏል።


በትግራይ ያለው የኤችአይቪ ስርጭትለመዳሰስ በክልሉ ጤና ቢሮ እና አጋዥ አካላት ተሳትፎ፥ ካለፈው ግንቦት እስከ መስከረም 2017 ዓመተምህረት የተካሄደ ጥናት እንደሚያመለክተው ከትግራይ ቫይረሱ ስርጭት በእጥፍ መጨመሩ ያሳያል። እንደ የትግራይ ጤና ቢሮ ገለፃ ከሀያ ዓመት በፊት በክልሉ የነበረው የኤችአይቪ ስርጭት መጠን፥ አሁን ላይ ካለው ጋር ሲነፃፀር በዚህ ወቅት ከፍተኛ ነው የሚል ሲሆን፥ ከጦርነቱ በፊት በትግራይ የነበረው 1 ነጥብ 2 ከመቶ የቫይረሱ ስርጭት አሁን ላይ 3 ከመቶ መድረሱ በጥናት ተረጋግጧል። በመቐለ፣ በትግራይ ደቡባዊ ዞን እንዲሁም በተፈናቃይ መኖርያ ጣብያዎች የስርጭት መጠኑ እስከ 6 ከመቶ እንደሚደርስም ተነግሯል።

በትግራይ የኤችአይቪ ኤድስ መከላከያ ስራ ላይ ከሚሰሩ የሀገር ውስጥ ተቋማት መካከል የሆነው ተስፋ ሕይወት ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ማሕበር አባል የሆኑት እና ላለፉት ከ20 በላይ ዓመታት ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩት ወይዘሮ አዝመራ አሸብር፥ በሚሰሩበት መቐለ ሆስፒታል በየቀኑ አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች በምርመራ እንደሚለዩ ይናገራሉ።

ኤችአይቪ በተመለከተ በህብረተሰቡ ዘንድ የግንዛቤ መውረድ፣ ጦርነቱ የፈጠረው ሁኔታ እንዲሁም የመከላከያ ግብአቶች እጥረት እና ሌሎች ውሱንነቶች በትግራይ የቫይረሱ ስርጭት እንዲባባስ ምክንያት መሆናቸው ተመልክቷል። የትግራይ ጤና ቢሮ ሐላፊ ዶክተር አማኑኤል ሃይለ "ከጦርነቱ በፊት በትግራይ የኤችአይቪ ስርጭት መጠን 1 ነጥብ 43 ከመቶ ነበረ። ይህ ማለት ከመቶ በትግራይ የሚኖሩ ከአንድ እስከ ሁለት በኤችአይቪ የተጠቃ ነበረ ማለት ነው። አሁን ባደረግነው ጥናት ግንየቫይረሱ ስርጭት ከእጥፍ በላይ ማደጉ ነው የሚያሳየን። ይህ በዝርዝር ስናየው በተለይም በሴተኛ አዳሪዎች ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ፣ እንደ ከአሁኑ በፊት በከተሞች የላቀ የቫይረሱ ስርጭት መታዩ ጥናቱ ያሳያል። ከዚህ በተጨማሪ ሴቶች እና ወንዶች ስናነፃፅር፥ የከፋ ተጠቂ ሆነው ያሉት ሴቶች ናቸው" ብለዋል።

በትግራይ ከዚህ ቀደም የነበሩ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችም መቀዛቀዛቸው ተነግሯል። በጦርነቱ ወቅት በትግራይ በቫይረሱ መከላከያ መድሃኒት እጦት ምክንያት በርካቶች ለሞት መዳረጋቸው የሚገልፁት የተስፋ ሕይወት ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ማሕበር አባልዋ ወይዘሮ አዝመራ አሸብር፥ አሁን ላይ የተወሰነ ለውጥ ቢኖርም ውሱንነቶች አሉ ይላሉ።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር