ማስታወቂያ
ብሌን እና መሠረት እዚህ ለመድረስ ካጋጠሟቸው ችግሮች መካከል ዋነኛው የማህበረሰቡ የተዛባ አመለካከት ነው ይላሉ ፡፡ በእግር ኳስ ተጫዋችነት ለመሳተፍ ባደረጉት ጥረት ሴት መሆናቸው ብቻውን ፈተናውን ከባድ እንዳደረገባቸውም አዳጊዎቹ ገልጸዋል፡፡ በተለይም ከአንዳንድ ሰዎች በጎ ያልሆኑ አስተያየቶች ይሰነዘሩባት እንደነበር የምትናገረው ብሌን ይህ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ሠርታ ለማሳየት ይበልጥ እንዳነሳሳት ትናገራለች ፡፡ መሠረት ደግሞ ከአሰልጣኝ እና ከሌሎች ተጫዋቾች ያገኘችው ምክር ቤተሰቦቿን እና ማህበረሰቡን ለማሳመን እንደረዳት ትናገራለች። የቡድናቸው አሰልጣኝ የሆኑት መሠረት ማኔ« የልጆቹ ህልም እንዲሳካ የክለብ ወይም የአሰልጣኝ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የህብረተሰብ፣ የቤተሰብ እና የመንግሥትም ኃላፊነት ነው ይላሉ። #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘጋቢ ፡ ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ ፡ ሸዋንግዛው ወጋየሁ