ማስታወቂያ
ወጣት ራሄል በትምህርት ቤት ደረጃ ታደርገው የነበረው ጥረት ለአትሌቲክ ስፖርት ጅማሮዋ መነሻ እንደሆናት ተናግራለች ፡፡ ወጣት ራሄል በተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ውድድሮች አገሯን በመወከል መወዳደሯንና በዚህም የተሻለ ውጤት ማስመዝገቧን ገልጻለች ፡፡ ውድድሮቹ በራስ የመተማመን ብቃት ለመፍጠር እንዳስቻሏትና አሁን ላይ አሉ ከሚባሉ አትሌቶች ተርታ ለመሰለፍ እንዳበቃት ጠቅሳለች ፡፡
በአሁኑ ወቅት በመቻል የአትሌቲክስ ስፖርት ክለብ ውስጥ በቋሚ ተወዳዳሪነት እየሠራች እንደምትገኝ የጠቀሰችው ራሄል አሁን ለደረሰችበት ደረጃ ለመብቃት የቤተሰቦቿ እና የአሠልጣኞቿ ድጋፍ ትልቅ እንደሆነም ተናግራለች ፡፡
ማንኛውም ዓላማ የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የጠቀሰችው ራሄል በተለይ በአጭር ርቀት ስፖርት ብዙ ፈተናዎች ያጋጥማሉ ብላለች ፡፡
በቀጣይ የአትሌቲክስ ብቃቷን ከፍ በማድረግ የአገሯን ሥም በዓለም አደባባይ የማስጠራት ግብ እንዳላት ወጣት ራሄል ተናግራለች ፡፡ ወጣት ሴቶች ካሰቡበት ለመድረስ ሁሉንም ነገር በትዕግሥት ከታች መጀመርና በሂደት ሊጋጥሟቸው የሚችሉ ችግሮቹን ለመጋፈጥ መዘጋጀት አለባቸው ትላለች፡፡ #GirlzOffMute #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች
ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ