ማስታወቂያ
በአብዛኛው የምታስተላልፋቸው መልዕክቶች በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩና እያዝናኑ የሚያስተምሩ መሆናቸው የጠቀሰችው ብሌን “ ሰዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ይሰጡኛል ፡፡ በተለይ እማማ ዝናሽ የሚባሉ አናትን አስመስዬ ሥለምጫወት ብዙዎች በስሜ ሳይሆን “ እማማ ዝናሽ “ እያሉ ነው የሚጠሩኝ ፡፡ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ እና የሰፈር ጎረቤቶች ሥራዎቼ ጥሩ መሆናቸውን በመገልጽ ያበረታቱኛል “ ብላለች ፡፡
“ ቲክቶክ ለመሥራት የምጠቀመው ጊዜ አነስተኛ መሆኑ በትምህርቴ ላይ ተፅኖ አላሳደረብኝም “ የምትለው ብሌን “ወደፊት ከቲክቶክ ሥራው ጎን ለጎን የህክምና ዶክተር የመሆን ህልም አለኝ ፡፡ በእኔ ዕድሜ የሚገኙ ታዳጊዎች በውስጣቸው ያላቸውን ችሎታ አውጥተው መጠቀም አለባቸው ፡፡ ቤተሰቦቻቸውም ልጆችን መደገፍና ማበረታታት አለባቸው “ ብላለች ፡፡እስካሁን ከዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት እንግዶች በእድሜ ትንሿ የሆነችው ብሌን ታገል። #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ:ሸዋንግዛው ወጋየሁ