1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አርቃቂ ባለሙያዎች ምን እየሠሩ ይኾን ?

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 30 2015

በፍትሕ ሚኒስቴር 14 አባላትን ይዞ የተቋቋመው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አርቃቂ የባለሙያዎች ቡድን ከአዲስ አበባ በስተቀር በሁሉም ክልሎች በጉዳዩ ላይ ከሕዝብ ጋር ውይይት ማድረጉን ገለፀ።

https://p.dw.com/p/4VyhD
Dr. Marshet Tadesse , Ato Misganaw Mulugeta, Dr. Tadesse Kassa
ምስል Solomon Muchie/DW

የሽግግር ፍትኅ ፖሊሲ የማርቀቁ ስራ ከምን ደርሶ ይኾን?

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አርቃቂ ባለሙያዎች ምን እየሠሩ ነው ?


በፍትሕ ሚኒስቴር 14 አባላትን ይዞ የተቋቋመው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አርቃቂ የባለሙያዎች ቡድን ከአዲስ አበባ በስተቀር በሁሉም ክልሎች በጉዳዩ ላይ ከሕዝብ ጋር ውይይት ማድረጉን ገለፀ።
የፖሊሲ ማርቀቅ ቅድመ ውይይት ሂደት ላይ መሆኑን የገለፀውና ከተቋቋመ ዘጠኝ ወራትን ያለፈው ይህ ቡድን እያከናወነ ያለው ሥራ ከብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ጋር የማይጋጭ ይልቁንም የሚመጋገብ መሆኑን ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።ምክክር በሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ ሰነድ ላይ

ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፣ አለመረጋጋት፣ ግጭትና የእርስ በርስ ጦርነት መቀጠሉ ዜጎች ለሞት፣ ለመፈናቀል አደጋ እየተጋለጡ በመሆኑና ለነዚህ ችግሮች ከዚህ በፊት የተሰጡ ምላሾች ሙሉ አለመሆባቸው የአጥፊዎችና የተጎጅዎችን ቁጥር ማብዛቱ ፣ የበደሎች መደራረብ እና የጥፋቶች ማህበረሰባዊ ቅርጽ መያዝ በመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት እና አካሄድ ፍትሕ መስጠትንም ሆነ ይቅርታ እና እርቅን ማከናወን አላስችል ማለቱ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና እርቅን ለመስጠት የሽግግር ፍትሕ አስፈላጊ መሆኑን መንግሥት እንዳመነበት ከዚህ በፊት አስታውቋል።

የሽግግር ፍትሕ አስፈላጊነት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት በሽግግር ሁኔታ ውስጥ ብታልፍም  ውጤታማ እንዳልነበር መገንዘቡን የገለፀው የኢትዮጵያ መንግሥት ሀሳቡ በግጭት፣ በጦርነት ወይም በሌላ ምክንያት ለተፈፀመ ጥቃት ፣ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በደሎች የተሟላ መፍትሔ መስጠት መሆኑን እና ውጤቱ ዘላቂ ሰላም ፣ እርቅ፣ መረጋጋት እና የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት መፍጠር መሆኑንም የባለሙያዎችን ቡድን አዋቅሮ ወደ ሥራ ሲገባ ገልጿል።በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህና ፍኖተ ካርታ ላይ ውይይት ይካሄዳል ተባለ
እውነት እየተጣራ ይፋ የሚሆንበት ፣ እርቅ የሚሰፍንበት፣ የማካካሻ እርምጃ እና የተቋማት ለውጥ የሚካሄድበት ይሆናል የተባለለትን የፖሊሲ ሰነድ እያዘጋጁ ያሉት ባለሙያዎች የጉዳዩን አስፈላጊነት በሁሉም ክልሎች አደረግን ባሉት ውይይት መገንዘባቸውን ከባለሙያዎቹ አንዱ የሆኑትዶክተር ማርሸት ታደሰ ገልፀዋል።
"ኢትዮጵያ ይነስም ይብዛም ግጭት ውስጥ ነው ያለችው ። ስለዚህ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ለሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፉ የምናደርገው ሂደት ተገቢ ነው ወይ የሚሉ የሚነሱልን ፣ እኛም ክልል ላይ ሄደን ሕዝቦችን በምናወያይበት ጊዜ አንዱ የሚነሳልን ጥያቄ ነበር። ካደረግነው ግብዓት የማሰባሰብ ሂደት ግን አንዱ የተረዳነው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዘጋጀት እና መተግበር አስፈላጊ መሆኑን አብዛኛው ያወያየነው ሰው ግልጽ በሆነ ሁኔታ ይነግረናል" ።

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ከምክክር ኮሚሽን ሥራ ይለያልን
ፍትሕ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፣ አለመረጋጋት፣ ግጭትና የእርስ በርስ ጦርነት በመቀጠሉ ዜጎች ለሞት፣ ለመፈናቀል አደጋ እየተጋለጡ በመሆኑና ለነዚህ ችግሮች ከዚህ በፊት የተሰጡ ምላሾች ሙሉ አለመሆናቸው የአጥፊዎችና የተጎጅዎችን ቁጥር ማብዛቱ ፣ የበደሎች መደራረብ እና የጥፋቶች ማህበረሰባዊ ቅርጽ መያዝ በመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት እና አካሄድ ፍትሕ መስጠትንም ሆነ ይቅርታ እና እርቅን ማከናወን አላስችል በማለቱ ፣ ባለፉ በደሎች ይቅር ለመባባልና እርቅ ለማውረድ ብሎም የተከፋፈለ ያለውን ሕዝብ ለማቀራረብ ግንኙነትን ለመጠገን፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና እርቅን ለመስጠት፣ የተሳካ የሽግግር ፍትሕ ሂደት ሳይተገበር የዴሞክራሲ ሽግግርም ሆነ ዘላቂ ሰላም ማስፈን ስለማይቻል እንዲሁም ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን በሚል ይህንን ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።ያለተጠያቂነት ዘላቂ ሰላም እንዴት? ይህ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ከሚሠራው በምን ይለያል በሚል ክርክርና ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም። የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አርቃቂ ባለሙያዎች ቡድን አባል የሆኑት አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ ለዚህ ምላሽ ሰጥተዋል።
" ሀገራዊ የሆኑ፣ ለዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩ ቁርሾዎችን ፣ ልዩነቶችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በግልጽ እውነትን በማውጣት፣ ውይይት በማድረግ እና መሰረታዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን በማንሳት አገረ መንግስቱ ጠንካራ መሠረት ላይ እንዲወድቅ በፍትሕ ላይ ፣ በውይይት ላይ፣ በዴሞክራሲ ላይ የተመሰረተ አገረ መንግሥት ለመመስረት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ በሁለቱም ሂደቶች። ስለዚህ በዚህ ረገድ ተምሳሳይነት አላቸው"

የሽግግር ፍትሕ አተገባበር ተስፋ እና ሥጋት
ኢትዮጵያዊ ተነሳሽነት ለሰብዓዊ መብቶች የተባለ ሀገር በቀል ሲቪል ድርጅት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ሰለሞን በጉዳዩ ላይ ከዚህ በፊት ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት የሽግግር ፍትሕ እጅግ አስፈላጊ ነው ሆኖም አተገባበሩ ካልተሳካ አደጋው የከፋ ነው ብለው ነበር።የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ
ፍትሕ ሚኒስቴር በባለሙያዎች እያዘጋጀው ያለው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማስፈፀሚያ ስልቶች ብሎ ካስቀመጣቸው ጉዳዮች ክስ ፣ እውነትን ማፈላለግ እና ይፋ ማድረግ፣ እርቅ ፣ ምህረት፣ ማካካሻ ይገኙበታል። የባለሙያዎች ቡድን የፀጥታ ሥጋት በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የሥራችን እንቅፋት ሆነዋል ሲል ገልጿል።
ሥራው ሲጠናቀቅ ለሚከተለው የትግበራው ሂደት አንፃራዊ ሰላም ያስፈልጋል ያሉት ባለሙያዎቹ ሥራችንን "ግልፀኝነት እና ገለልተኝነት በተሞላበት በነፃነት" እየሠራን ነው ብለዋል።

 ዶ/ር ማርሸት ታደሰ፣ አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ ፣ ዶ/ር ታደሰ ካሳ  በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል
እውነት እየተጣራ ይፋ የሚሆንበት ፣ እርቅ የሚሰፍንበት፣ የማካካሻ እርምጃ እና የተቋማት ለውጥ የሚካሄድበት ይሆናል የተባለለትን የፖሊሲ ሰነድ እያዘጋጁ ያሉት ባለሙያዎች የጉዳዩን አስፈላጊነት በሁሉም ክልሎች አደረግን ባሉት ውይይት መገንዘባቸውን ከባለሙያዎቹ አንዱ የሆኑትዶክተር ማርሸት ታደሰ ገልፀዋል።ምስል Solomon Muchie/DW
የኢትዮጵያ የፍትሕ ሚኒስቴር
በፍትሕ ሚኒስቴር 14 አባላትን ይዞ የተቋቋመው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አርቃቂ የባለሙያዎች ቡድን ከአዲስ አበባ በስተቀር በሁሉም ክልሎች በጉዳዩ ላይ ከሕዝብ ጋር ውይይት ማድረጉን ገለፀ።ምስል Solomon Muchie/DW
 ዶ/ር ማርሸት ታደሰ፣ አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ ፣ ዶ/ር ታደሰ ካሳ  በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል
የበደሎች መደራረብ እና የጥፋቶች ማህበረሰባዊ ቅርጽ መያዝ በመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት እና አካሄድ ፍትሕ መስጠትንም ሆነ ይቅርታ እና እርቅን ማከናወን አላስችል ማለቱ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና እርቅን ለመስጠት የሽግግር ፍትሕ አስፈላጊ መሆኑን መንግሥት እንዳመነበት ከዚህ በፊት አስታውቋል።ምስል Solomon Muchie/DW

ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ