ዉይይት፤ የተቃዋሚዎችና የገዥዉ ፓርቲ ድርድር
እሑድ፣ ጥር 21 2009ማስታወቂያ
በቅርቡ የተደረገዉ የተቃዋሚዎችና የገዥዉ ፓርቲ ዉይይትም በዚሁ በመንግስት እቅድ ላይ የተመሰረተ ነዉ። ዉይይቱ የመነጋገርያ አጀንዳ ለመቅረጽ እና ሃሳቦችን ለመለዋወጥ የተደረገ መሆኑ ከመነገሩ ዉጭ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች እንዳልተነሱበት ተሳታፊዎች ይናገራሉ። አንዳንድ ታዛቢዎች ዉይይቱ ለወደፊቱ ተቃዋሚዎችን ከገዥዉ ፓርቲ ጋር ለማቀራረብ ይጠቅማል ይላሉ። የዛኑ ያክል ዉይይቱን በርካታ ተቃዋሚዎች በተለይም መቀመጫቸዉን ከኢትዮጵያ ዉጭ ያደረጉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ያገለለ በመሆኑ ሁሉን አካታች አይደለም ሲሉ ትችት የሚያሰሙ አሉ። በሌላ በኩል መንግሥት በዉይይቱ የሥነ-ምግባር ደንብ ካልፈረሙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ጭምር እንደሚወያይ ገልጾአል። ይህ ዝግጅታችን የተቃዋሚዎችና የገዥዉ ፓርቲ ዉይይት ያስነሳዉ ክርክርና ፖለቲካዊ ፋይዳዉን ያስቃኛል። በዉይይቱ ላይ የተሳተፉት ዶ/ር ጫኔ ከበደ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዎ ፓርቲ «ኢዴፓ» ፕሬዚዳንት ፤ አቶ ሙሉጌታ አበበ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት «መኢአድ» ሃላፊነት ምክትል ፕሬዚዳንት፤ ዶ/ር ተሾመ ታፈሰ የአመራርና አስተዳደር ተቋም መምህር፤ እንዲሁም አቶ ዩሱፍ ያሲን የፖለቲካ ተንታኝ ናቸዉ። ሙሉ ዉይይቱን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።
አዜብ ታደሰ
ልደት አበበ