1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት ለዩክሬን ዘላቂ ድጋፉ ይቀጥላል አለ

ማክሰኞ፣ መስከረም 22 2016

27ቱ የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጦርነት ውስጥ በሆነችው የኪየቭ ከተማ ትናንት ተሰብስበው ለዩክሬን የሚሰጡትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። የሚኒስትሮቹ ስብሰባ በዩክሬን ኪየቭ ከተማ መደረጉ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ተብሏል ።

https://p.dw.com/p/4X4qV
27ቱ የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በዩክሬን ኪዬቭ ከተማ
27ቱ የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጦርነት ውስጥ በሆነችው የኪየቭ ከተማ ትናንት ተሰብስበው ለዩክሬን  የሚሰጡትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ምስል Ukrainian Presidential Press Service/REUTERS

የአውሮጳ ኅብረት ስብሰባ የተደረገው በዩክሬን ነው

የአውሮጳ ኅብረት ለዩክሬን የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል በማስታወቅ በጦርነት የተዳቀቀችው ሀገር የኅብረቱ አባል እንደምትሆን ትናንት ባደረገው ስብሰባ ዐስታውቋል ። ዩክሬንከኅብረቱ ከ5 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ወታደራዊ ርዳታ ይሰጣታልም ተብሏል ። ለሩስያ የምታደላው ሐንጋሪ ለዩክሬን ድጋፍ መጠናከሩን ተቃውማለች ። ኅብረቱ ማናቸውም ውሳኔ ለማሳለፍ 27ቱም አባል ሃገራት በሙሉ ድምፅ መወሰን ይገባቸዋል ። የአውሮጳ ኅብረት ሚኒስትሮች ስብሰባቸውን በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ማድረጋቸውም ትልቅ ትርጉም ያለው ተብሎለታል ። ሩስያ በበኩሏ ባለፉት ዐሥር ወራት ብቻ ከ335,000 በላይ ሰዎች የጦር ሠራዊት አባል ለመሆን ተመዝግበዋል፤ ለረዥም ጦርነትም ዝግጁ ነኝ ብላለች ። 

27ቱ የአውሮጳ ኅብረት የውጭ  ጉዳይ ሚኒስትሮች በጦርነት ውስጥ በሆነችው የኪየቭ ከተማ ትናንት ተሰብስበው ለዩክሬን  የሚሰጡትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። የሚኒስትሮቹ ስብሰባ በዩክሬን ኪየቭ ከተማ  መደረጉ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን የስብሰብው መሪና የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሚስተር ጆሴፕ ቦርየል  ሲገልጹ፤ «በበርካታ ምክንያቶች ይህ ስብሰባ ታሪካዊ ነው። ከህብረቱ ውጭ የተካሄደ የመጀመሪያ ስብሰባ ነው፤ በዕጩ አባል ያውም ጦርነት እየተከሂደበት ባለ አገር የተካሄደ የመጀመሪያ የህብረቱ ስብሰባ ነው» በማለት በዚህም ሚኒስትሮቹ ለዩክሬን የአንድነትና ድጋፍ መልእክት ያስተላለፉ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአውሮጳ ኅብረት በዩክሬን ኪዬቭ ስብሰባ
የአውሮጳ ኅብረት ለዩክሬን የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ዐስታውቋልምስል Ukrainian Presidential Press Service/REUTERS

ሚኒስትሮቹ በስብሰባቸው ከዩክሬኑ ፕሪዘዳንት ቮሎድሚየር ዘለንስኪና የውጭ ጉድይ ሚኒስትራቸው ሚስተር ኩሌባ  ጋር በነበራቸው ውይይት ህብረቱና አባል አገራቱ በቀጣይ ሊያደረጉ ስለሚችሉት ድጋፍና ሊሰጡ ስለሚችሉት እርዳታ በሰፊው መወያየታቸው ተገልጿል። ሚስተር ቦርየል በጋዜጣዊ መግለጫቸው እንዳብራሩት፤ ስብሰባው አባል አገሮች ለዩክሬን የሚሰጡትን ርዳታ ለመቀጠል ቁርጠኝነት ያሳዩበት ነው።የህብረቱ አገሮች የዩክሬን ወታደሮችን ማሰልጠን እንደሚቀጥሉና በሚቀጥሉት ወራት ውስጥም 40 ሺ ወታደሮችን እንደሚያሰለጥኑ ሚስተር ቦርየል አስታውቀዋል፡፤ ከሁሉም በላይ ግን አሉ ሚስተር ቦርየል፤ ከሁሉም በላይ ለዩከሬን ደህንነት የምንሰጠው ዋስትና  " ለዩክሬን የምንሰጠው ትልቁ የደህንነት ዋስትና፤ የህብረቱን አባልነት ነው” በማለት በአሁኑ ወቅት ዩኪረን እጩ አባል አገር መሆኗን አስታውቀዋል። ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በሰላም ጉዳይም እንደተወያዩና የፕሬዝዳንት ዘለንስኪን የሰላም ሀሳብ በጥልቀት እንዳዩት ሚስተር ቦርየል አክለው ገልጸዋል፡፤ እስካሁን ከቀረቡት የሰላም እቅዶችም የተሻለው የሚስተር ዘለልንስኪ የስላም ሀስብ መሆኑን ሚኒስትሮቹ እንደተገንዘቡት ጭምር ሚስተር ቦርየል በመግለጫቸው አስርግጠው ተናግረዋል።

የፕሬዝዳንት ዘለርንስኪ የሰላም ሀሳብ በዋናነት በቅድሚ ሩሲያ ክሬሚያን ጨምሮ ከያዘችቻቸው የዩክሬን ግዛቶች እንድትወጣ የሚጠይቅ መሆኑ ይታወቃል። ይህን ሀስብ ሩሲያ ባትቀበለውም በህብረቱ በኩል ግን ትክክለኝውና ብቸኛው የጦርነቱ መውጫ ሆኖ እንድተወሰደ ነው እይተገልጸ ያለው። ሌሎች አገሮች ለምሳሌ ቻይናና ደቡብ አፍርካ፤ ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን አቁመው የሰላም አማራጮችን እንዲፈልጉ በመጠየቅ የየበኩላቸውን የሰላም ሀሳቦች አቅርበው የነበር መሆኑም አይዘነጋም።

የአውሮጳ ኅብረት በዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ
የአውሮጳ ኅብረት በዩክሬን ዋና ከተማ ኪዬቭ ታሪካዊ የተባለውን የኅብረቱን ስብሰባ አድርጓልምስል Ukrainian Presidential Press Service/REUTERS

ይህ የህብረቱ ሚኒስትሮች ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍየገለጹበትና ታርካዊ የተባለው ስብሰባ በኬይቭ ከመካሄዱ በፊት ትቂት ቀናት ቀደም ብሎ ግን፤ የአሜርካ ምክርቤት በጀቱን ሲያጸድቅ ለዩክሬን ተይዞ የነበረውን 6 ቢልዮን ዶላር እንዲዘገይ ማድረጉና በህብረቱ አባል አገር ስሎቫኪይ በተካሄደ ምርጫ፤ ለዩክሬን የሚላከውን የጦር መሳሪያ በመቃወም ዘመቻ ሲይደርግ የነበረ ፓርቲ ማሸነፉ፤ የዩኪሬን ወዳጆችን  አንድነት ዘላቂነት የሚያጠያይቅ ሁኗል። የዩክሬኑ የውጭ ጉዳያ ሚኒስተር ሚስተር ኩሌባ የስሎቫኪያው የምርጫ ውጤት ለዩክሬን በሚደረገው እርዳታ ላይ ስለሚያሳድረው ተጽኖ አሁን መናገር እንደማይቻል አውስተው፤ የሚቁቁመውን መንግስት መጠበቅ እንደሚይስፈልግ አሳስበዋል።  የአሜሪካንንን የምክርቤት ውሳኔ በሚመለክት ሲናገሩ ግን " ጥያቄው መሆን ያለበት አሁን በአሜሪካ ምክር ቤት የሆነው ቋሚ ነው ወይንስ ግዚያዊ የሚለው ነው። እንደሚመስለኝ ግዚያዊ ነው። ከሁሉም የምክርቤት ቡድኖች ጋር በሰፊው  ተወያይተናል” በማለት አሚሪካኖቹ የየክሬኑ ጦርነት ከዩክሬን የዘለለ መሆኑን የሚረዱትና የሚያውቁት የመስለኛል ሲሉ ውጊያው ስለዓለም ሰላምና መረጋጋት መሆኑን እንደሚገንዘቡትና እርድታቸውም ይቋረጣል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል።

ሚስተር ቦርየል በበኩላቸው ጦርነቱ ለዓለም ሰላም ጭምር በመሆኑ አሜሪካኖቹ ውሳኔያቸውን ደግመው እንደሚያዩት ተስፋ እንደሚያደርጉ ጠቅሰው፤ ለአውሮፓውያን ግን የህልውና ስጋት የፈጠረ እንደሆነና በዚህም ምክኒያት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ