1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 29 2016

የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን አስፈፃሚው አካል ላይ ጫና በማድረግ እንዲያግዘው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጠየቀ። ኮሚሽኑ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለፉት አራት ወራት የሥራ አፈፃፀሙን ሲያቀርብ መንግስትም ሆነ ጫካ ገብተው የሚዋጉ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ ምክር ቤቱ ጫና እንዲያደርግ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/4Ydev
ኮሚሽኑ "በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እየታዩ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች የኮሚሽኑን ሥራ አዳጋች እያደረጉት ይገኛሉ" ሲል በመግለጫው ማስታወቁም ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "የሚታዩ ግጭቶች በአስቸኳይ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ቆመው የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ አሉን የሚሏቸውን ልዩነቶች ወይም ጥያቄዎች በጠረንጴዛ ተቀምጠው በምክክር እንዲፈቱ" ሲል አስቸኳይ ያለውን ሀገራዊ ጥሪ ከጥቂት ወራት በፊት አቅርቧል። ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ

ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረበው ዘገባው በሚጠበቀው ምክክር ውስጥ በየቦታው የሚገኙ ተፈናቃዮች እንደ አንድ ባለድርሻ አካል እንዲታዩ ይደረጋል ብሏል። ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ከፍተኛ የመፈናቀል ችግር ባለባት ኢትዮጵያ የተፈናቃዮች የተሳትፎ ጉዳይ ራሱን ችሎ ትልቅ ሀገራዊ አጀንዳ ሊሆን የሚገባው መሆኑን ጠቁመዋል። በማንነታቸው እና በሥራቸው ምክንያት የተገለሉ እና የተገፉ የማህበረሰብ ክፍሎችም በዚህ ምክክር ሊካተቱ ይገባል ብሏል።
ተቋማት፣ ማሕበራት እንዲሁም መንግሥት እንደየደረጃቸው ጉልህ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይደረጋልም ተብሏል። ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታ ስልጠና በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች መስጠቱንና በቀጣይ የምክክር አጀንዳ የማሰባሰብና የመቅረጽ ሥራ እንደሚያከናውን አስታውቋል።የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስቸኳይ ሀገራዊ ጥሪ


ከምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ቀርበዋል። "የኢትዮጵያ ሕዝብ በኮሚሽኑ ላይ ጥሎት የነበረው ተስፋ ሳይመናመን ተጨባጭ እንቅስቃሴ ተደርጎ በአጭር ጊዜ ውጤት መመዝገብ አለበት" ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ለዚህ ምላሽ ሰጥተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ማነስ፣ የመተማመን ችግር ፣ በውይይት ወቅት ሊኖር የሚችል የፖለቲካ ጫና ሥጋት እና ሌሎች ጥያቄዎች ከኮሚሽኑ ቀርበዋል። ዋናው ውይይት መቼ ይጀመራል የሚለው ጥያቄ ዛሬም ተጠይቋል።ምክትል ዋና ኮሚሽነር ኂሩት ገብረ ሥላሴ ሥራው ሰፊ ከመሆኑ አንፃር እና በሌሎች ችግሮች ኮሚሽኑ በእቅዱ ለመንቀሳቀስ እንደሚቸገር አብራርተዋል።የሽግግር ፍትሕ የሀገራዊ ምክክሩ ውጤት ሊሆን የሚገባው ጉዳይ ቢሆንም ከሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር መዘግየት ባለመቻሉ በቅርበት በመገናኘት ግጭት እንዳይፈጠር እየተመካከርን ለመሄድ ተነጋግረናል ብለዋል። ለሰላም የውይይት እና የመነጋገር ጥሪ

ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ከፍተኛ የመፈናቀል ችግር ባለባት ኢትዮጵያ የተፈናቃዮች የተሳትፎ ጉዳይ ራሱን ችሎ ትልቅ ሀገራዊ አጀንዳ ሊሆን የሚገባው መሆኑን ጠቁመዋል። በማንነታቸው እና በሥራቸው ምክንያት የተገለሉ እና የተገፉ የማህበረሰብ ክፍሎችም በዚህ ምክክር ሊካተቱ ይገባል ብሏል።
ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረበው ዘገባው በሚጠበቀው ምክክር ውስጥ በየቦታው የሚገኙ ተፈናቃዮች እንደ አንድ ባለድርሻ አካል እንዲታዩ ይደረጋል ብሏል። ምስል Solomon Muchie/DW

የተሰጠው የስልጣን ጊዜ አንድ ዓመት ከ 4 ወራት የቀረው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ግጭት እንዲቆም ምክር ቤቱ አስፈፃሚው ላይ ጫና እንዲያደርግ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ ጠይቀዋል።የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን "የሚታዩ ግጭቶች በአስቸኳይ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ቆመው የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ አሉን የሚሏቸውን ልዩነቶች ወይም ጥያቄዎች በጠረንጴዛ ተቀምጠው በምክክር እንዲፈቱ" ሲል አስቸኳይ ያለውን ሀገራዊ ጥሪ ከጥቂት ወራት በፊት አቅርቧል። ኮሚሽኑ "በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እየታዩ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች የኮሚሽኑን ሥራ አዳጋች እያደረጉት ይገኛሉ" ሲል በመግለጫው ማስታወቁም ይታወሳል።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ