ሰኞ፣ ታኅሣሥ 7 2017የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በምህጻሩ ኢሰመጉ ዋና ሃላፊ አቶ ዳን ይርጋ የሚደርስባቸው ወከባ በመባባሱ ምክንያት አገር ለቀው መሰደዳቸውን ድርጅቱ ለዶቼቬለ አረጋግጧል። በሌላ በኩል የኢትትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በሦስት ሀገር በቀል የሲቪክ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረው እገዳ መነሳቱ ታዉቋል።
ህወሓት በአንዳንድ አካባቢዎች አዳዲስ ሚሊሽያዎችን እየመለመለ ነው፣ በሕገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ላይም ተሰማርቷል ሲሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሰሱ።
ከ 3 ሺህ በላይ «የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ የባቡር መንገድ ፕሮጀክት» ሠራተኞች ያለፉት 9 ወራት ደሞዛችን አልተከፈለንም ሲሉ ለዶቼቬለ ተናገሩ።