ሰኞ፣ ጥቅምት 18 2017DW Amharic--ግብፅ አራት የሃማስ ታጋች እስራኤላውያንን በተወሰኑ ፍልስጤማዉያን እስረኞች ለመለወጥ በጋዛ የሁለት ቀን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሀሳብ አቀረበች። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኧልሲሲ ይህን ያሉት ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀውን የጋዛ ጦርነት ለማስቆም የሚደረገው ድርድር ድጋሚ በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡
--125 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሃገራቸዉ መመለሳቸዉን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
--የዩናይትድ ስቴትስ የሪፓብሊካን እጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ተቀናቃኛቸዉ የዲሞክራቶች እጩ ተወዳዳሪ ካማላ ሃሪስ ዩናይትድ ስቴትስን እያወደሙ ነዉ ሲሉ ከሰሱ ። ዝርዝሩን ያድምጡ!