1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመናዉያን በልዑል አስፋ ወሰን አስራተ እይታ

ሐሙስ፣ ጥር 16 2016

በቅርቡ ስለ ጀርመናዉያን ማንነት፤ ስለ ጀርመን ባህል ፤ ቋንቋና አኗኗር ብሎም ልማዳቸዉን ሁሉ የሚተርክ ፤መጽሐፍ በጀርመንኛ አሳትመዉ ለአንባቢ ያቀረቡት፤ በጀርመን የአፍሪቃ እና የመካከለኛዉ ምስራቅ ጉዳዮች አማካሪ፤ እንዲሁም የታሪክ ምሁሩ ልዑል ዶ/ር አስፋ ወሰን አስራተ መጽሐፉ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ ሰንብቷል።

https://p.dw.com/p/4bgOq
ስለጀርመናዉያን ባህል በልዑል አስፋ ወሰን አስራተ
ስለጀርመናዉያን ባህል በልዑል አስፋ ወሰን አስራተምስል Die Andere Bibliothek

ጀርመን እና ጀርመናዉያን ፤ ከልዑል አስፋ ወሰን አስራተ ጋር

በቅርቡ ስለ ጀርመናዉያን ማንነት፤ ስለ ጀርመን ባህል ፤ ቋንቋና አኗኗር ብሎም ልማዳቸዉን ሁሉ የሚተርክ ፤መጽሐፍ በጀርመንኛ አሳትመዉ ለአንባቢ ያቀረቡት፤ በጀርመን የአፍሪቃ እና የመካከለኛዉ ምስራቅ ጉዳዮች አማካሪ፤ እንዲሁም የታሪክ ምሁሩ ልዑል ዶ/ር አስፋ ወሰን አስራተ  መጽሐፉ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ ሰንብቷል። በግርድፉ ጀርመን ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር የሚል ትርጓሜ ያለዉ እና በዉስጡ ሀ ለ ሐመ እያለ በተርታ በረድፍ የጀርመናዉያን የአመጋገብ ሥነ-ስርዓት፤  ልማድ ባህሪ፤ ቋንቋ እና ልዩ የጀርመን ቃላቶችን እና አገላለጾችን የሳዩበት መጽሐፍ  ለአንባብያን ከደረሰ በኋላ በጀርመን የተለያዩ ጋዜጦች እና ሚዲያዎች ልዑል አሳፋወሰን አስራተ ስለጻፉት መጽሐፍ ብዙ ጽፈዋል፤ ልዑሉም በተለያዩ የቴሌቭዝን ማሰራጫዎች እና ራድዮ ጣብያዎች እየተጋበጡ ስለመጽሐፋቸዉ ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል።  በቅርቡ ልዑል አስፋወሰን አስራተ WDR ለተባለዉ ለታዋቂዉ የጀርመን ሬድዮ ጣብያ ስለአዲሱ መጽሐፋቸዉ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ በጀርመን ይበልጥ አገር ወዳድነትን እንዲታይ መመኘታቸዉን ጽፏል። ጀርመንኛን እንደ ትዉልድ ቋንቋቸዉ የሚናገሩት ልዑል አስፋ ወሰን በቅርቡ በጀርመንኛ ለአንባቢ ያቀረቡት ዶች ፎም ሻይትል ቢስ ዙር ዞለ Deutsch vom Scheitel bis zur Sohle የተሰኘዉ መጽሐፋቸዉ ርዕሱ ምን ለማለት ነዉ ስንል ነበር ወደ ዝግጅት ክፍላችን የጋበዝናቸዉ።  

መጽሐፉን ልከዉልኝ እኔም አይቸዋለሁ፤ ዉስጡ ስለ ጀርመናዉያን፤ አመጋገብ ፤ ስራ፤ ባህል ቋንቋ አጠቃቀም የመሳሰሉ ነገሮችን በረድፍ አድርገዉ በሚገርም አገላለጽ አስቀምጠዋል።  

ጀርመናዉያን ሰዓት አክባሪዎች፤ በዲሲፕሊን የተሞሉ፤ ድንገቴ የሆነ ነገር የማይሰሩ፣ አስበዉ አድረዉበት ማለት አሳድረዉ የሚወስኑ፤ ብሎም በደስታ የማይቦርቁ ፤ ቀልድም ብዙ የማያዉቁ ፤ የሚል የጥቅል መለያ ሲሰጣቸዉ ይሰማል።  

የቀድሞ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የቤተሰብ አባል የሆኑት ልዑል አስፋወሰን አስራተ በጀርመን ሲኖሩ ከሃምሳ ዓመታት በላይ የሆናቸዋል። በቅርቡ የ 75 ኛ ዓመት የልደት ቀናቸዉንም አክብረዋል። ልዑል አስፋ ወሰን አስራተ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የዘውዳዊው አስተዳደር ምክር ቤት፤ ፕሬዝዳንትና የኤርትራ ክፍለ ሃገር እንደራሴ  የልዑል ራስ አስራተ ካሳ እና የባለቤታቸዉ ልዕልት ዙሪያሽ ወርቅልጅ ናቸዉ። በጀርመን እና በብሪታንያ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን አጠናቀዉ የዶክትሬት ማዕረግንም ተቀብለዋል። ልዑል አስፋ ወሰን በጀርመን የአፍሪቃ እና የመካከለኛዉ ምስራቅ ጉዳዮች አማካሪ ሆነዉ ያገለገሉት የታሪክ ምሁሩ በጀርመን አስራ አንድ መጻህፍትን ለአንባቢያን አቅርበዋል።   

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ