1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የአማራ ክልል ጦርነት ማብቂያው የት ነው?

እሑድ፣ ነሐሴ 12 2016

አንድ ዓመት ባለፈው የአማራ ክልል ጦርነት ከሁለቱም ወገን ፣ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የሰዎች ሕይወት እንደጠፋ በርካታ ንብረትም እንደወደመ በሰላማዊ ሰዎች ላይም የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ሴቶችንም የወሲብ ጥቃቶች ሰለባ ማድረጉን የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችባወጧቸው ዘገባዎች አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/4jaUX
በአማራ ክልል በጦርነት የወደመ ወታደራዊ ተሽከርካሪ
በአማራ ክልል በጦርነት የወደመ ወታደራዊ ተሽከርካሪምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance

ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የአማራ ክልል ጦርነት ማብቂያው የት ነው?

በአማራ ክልል የሚካሄደው ጦርነት ወደ ሁለተኛው ዓመት ተሻግሯል።የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በክልሉ የሚገኙ ታጣቂ ኃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታትና ልዩ ኃይሉንም ለመበተን ባለፈው ዓመት ሐምሌ ከወሰነ በኋላ የተጀመረው ይህ ውጊያ ክልሉን ለተለያዩ ቀውሶች መዳረጉን ነዋሪዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ይናገራሉ ።

በአማራ ክልል አንድ ዓመት ባስቆጠረው ጦርነት ነዋሪዎች ምን አሉ ?

በክልሉ የመንግሥትን ውሳኔ የተቃወሙ ኃይሎች እንቅስቃሴ ሲበረታ የክልሉ መንግሥት የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንዲገባ ከጠየቀ በኋላ በክልሉ በተሰማራው በፌደራል መንግሥት ኃይልና በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተደራጁ የፋኖ ኃይላት መካከል ሲካሄድ በቆየው ከባድ ውጊያ ብዙ ኪሳራ ደርሷል።

 

የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በውጊያው ከሁለቱም ወገን የሰዎች ሕይወት እንደጠፋ በርካታ ንብረትም እንደወደመ በሰላማዊ ሰዎች ላይም የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ሴቶችንም የወሲብ ጥቃቶች ሰለባ ማድረጉን ባወጧቸው ዘገባዎች አስታውቀዋል።

  

በአማራ ክልል አዊ ዞን ከአንድ ዓመት በፊት ትጥቅ ፈቱ የተባሉ ሚሊሽያዎች
በአማራ ክልል አዊ ዞን ከአንድ ዓመት በፊት ትጥቅ ፈቱ የተባሉ ሚሊሽያዎችምስል Awi zone communication office

የአማራ ክልል መንግሥት «ህወሓት ጦርነት ከፍቶብኛል» አለ

ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የአማራ ክልል ጦርነት ማብቂያው የት ነው? የዛሬው እንወያይ የመነጋገሪያ ርዕስ ነው። በዚህ ርዕስ ላይ የየሚወያዩ አራት እንግዶችን ጋብዘናል እነርሱም ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ በአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝም መምህርና የሰብዓዊ መብት ረዳት ፕሮፌሰር፣ አቶ ሲሳይ አሳምሬ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የፖለቲካና የፍልስፍና ረዳት ፕሮፌሰር ፣ አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም አቶ እያቸው ተሻለ ለአማራ ክልል ግጭት መፍትሄ ለማፈላለግ የተቋቋመው «የሰላም ካውንስል» የህዝብ ግንኙነት ናቸው።ሙሉውን ውይይት ለመከታተል ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ

ኂሩት መለሰ