1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሰመጉ የእስረኞችን ሰብዓዊ መብት ይዞታ ለማየት ፈቃድ ተከለከልኩ አለ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 24 2016

የእስረኞችን አያያዝ ለማየት ፍቃድ ተከለከልኩ ሲል ቅሬታ ያሰማው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ ሁኔታው አሳስቦኛልም ብሏል። በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች በሕግ ከለላ ስር የሚገኙ እስረኞችን በተለይ የስብዓዊ መብት አያያዝን ለማየት ጥረት እያደርገ ቢሆንም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን ለጉብኘት ጥያቂ ምላሸ ባለማግኘቴ እንቅፋት ገጥሞኛል ብሏል ኢሰመጉ።

https://p.dw.com/p/4apMy
Logo des Ethiopian Human Rights Council
ምስል Ethiopian Human Rights Council

ኢሰመጉ የእስረኞችን ሰብዓዊ መብት ይዞታ ለማየት ፈቃድ ተከለከልኩ አለ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በተለያዩ ማረሚያ  ቤቶች እና ፖሊስ ጣቢያዎች  በእስር ላይ  የሚገኙትን እስረኞች  አያያዝ ለማየት  ቢጠይቅም የአዲስ አበባ መስተዳድር ፓሊስ እና የፌዴራል ፖሊስ ፍቃድ እንደከለከለው አስታውቀ ። የእስረኞች አያያዝ ለማየት  ፍቃድ ተከለከልኩ ሲል ቅሬታ ያሰማው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ ሁኔታው አሳስቦኛልም ብሏል። በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ በሕግ ከለላ ስር የሚገኙ እስረኞችን በተለየ የስብዓዊ መብት  አያያዝን ለማየት ጥረት እያደርገ  ቢሆንም ከቅርብ ግዜ ወዲህ  ግን ለጉብኘት  ጥያቂ ምላሸ ባለማግኘቴ እንቅፋት ገጥሞኛል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ  በምህጻሩ ኢሰመጉ አስታውቋል።የኢሰመጉ እና የመብት ተሟጋች ተቋማት ጥሪ 


የኢሰመጉ ዋና ሃላፊ አቶ ዳን ይርጋ  እሳቸው የሚመሩት  ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ   በሕግ የተቋቋመ እና ህጋዊ ፍቃድ ያለው ቢሆንም  በኢትዮጵያ ባሉ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ  የእስረኞችን  የሰብዓዊ መብት ይዞታን ለመመልከት እንዲፈቀድልን ደብዳቤ ብናስገባም ምላሽ ሳናገኘ  ከአንድ ወር በላይ ሆኖናል ሲሉ ለ DW ተናግረዋል። የመተከል ጥቃት፤ የኢሰመጉ መግለጫ እና የነዋሪዎች ስጋትለአዲስ አበባ ፣ፌደራል ፖሌሰ ፣ እና ለኦሮሚያ ክልል  የታራሚዎችን ስብአዊ መብት አያያዘ ልማት ጥያቄ ስታቀርቡ  ከዚህ በፊት ይሰጣቸሁ የነበረው ምላሽ ምን ይመስል ነበር  ከቅርብ ግዜ ወዲህ ገጠመን ያላቸሁት  እንቅፋት የተፈጠረበት  ምክንያት ምንድነው ሲል ዶቼቬለ አቶ ዳን ይርጋን ጠይቋል። አቶ ዳን በሰጡት ምላሽ ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ችግር ገጥሞዋቸው እንደማያውቅ  አሁን ግን ጥያቄው የቀረበላቸው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝምታን የመረጡ ይመስላል ብለዋል።

Äthiopien  Addis Ababa Ethiopian Federal police statement
ምስል Seyoum Getu/DW

 

የኢሰመጉ እና የመብት ተሟጋች ተቋማት ጥሪእስረኞችን ለመጎብኘት ፈቃድ አለመስጠት ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ እተካሄደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ብናቀርብም ጆሮ የሚሰጥ የለም ሲሉም ተናግረዋል።
የአዲሰ አበባ ፖሊሰ ህዘብ ግንኙነት ሀላፊ ኮማንደር ማርቆሰ ታደሰ ሰለጉዳዩ ለዶቼቬለ የሰጡት መልስ ለጊዜው መረጃ የለኝም የሚል ነው ። የአዲስ አበባ መስተዳድር የህዝብ ግንኙነት ምክትል ሀላፊ አቶ ብሩክ አበበ ጉዳዩ ከፖሊስ አልፎ የከተማዋ ቸግር ሆኖ እኛ ጋር የደረሰ ነገር የለም ሲሉ መልሰዋል ።

ሀና ደምሴ 
ኂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር