የተዘረፉ ቅርሶቻችንን ለመቀበል ዝግጁ ነን?
ሐሙስ፣ የካቲት 9 2015«የኢትዮጵያ የሆኑ ቅርሶች የጋራ መለያዎቻችን ናቸዉ። የጋራ ሃብቶቻችን ናቸዉ። በዉጭ በባዕድ አገር ሲቀሩ ልንቆጭ እና እኩል ልንቆረቆረ ይገባል። ምክንያቱም የሃገር ሃብት ናቸዉ እና።»የተዘረፉ የአፍሪቃ ቅርሶችን ለመመለስ ያለዉ ፍለጎት እስከምን?
በለንደን የኢትዮጵያ ቅርስ ማበልፀግያ ማህበር ዋና ስራስኪያጅ አቶ አለባቸዉ ደሳለኝ ከተናገሩት የተወሰደ ነዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 1897 ዓ.ም የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ወታደሮች በዛሬዋ ናይጄሪያ የበቤኒን ስርወ መንግሥት ቤተ መንግሥት ላይ ባካሄዱት ደም አፋሳሽ ወረራ ከዝሆን ጥርስ፣ እና ከነሐስ የተሠሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ቅርጻ ቅርጾችን ዘርፈዉ ለመላው አውሮጳ ሃገራት ሸጠዋል። በዝያን ጊዜ ከቤኒን ሥርወ መንግሥት የተዘረፉት እነዚህ ቅርሳ ቅርሶች በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለም ሃገራት ቤተ መዘክሮችም ይገኛሉ። በቅርቡ በጀርመን የሚገኙ ሙዚየሞች ከብሪታንያ ወታደሮች በጎርጎረሳዉያኑ 1897 ዓ.ም የገዝዋቸዉን እነዚህን የቤኒን ስርወ መንግሥት ቅርሳ ቅርሶች ከ 125 ዓመታት በኋላ ለናይጀርያ መንግሥት መመለስ ጀምረዋል። የጀርመንዋ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ በጀርመን ሃገር በሚገኙ ሙዚየሞች የሚገኙት እና በቁጥር ከ 1000 በላይ መሆናቸዉ የተነገረዉ የቤኒን ከመዳብ የተሰሩ ቅርሳ ቅርሶች መዘረፋቸዉ ስህተት ነዉ፤ ይህን ያህል ዓመታት ይዘን መቆየታችን ደግሞ ጥፋት ነዉ ሲሉ ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያኑ ዓመት መገባደጃ ላይ በናይጀርያ ተገኝተዉ የመጀመርያዉን ተመላሽ ቅርስ ባስረከቡበት ወቅት ተናግረዉ ነበር።
«ቅርሶቹ መዘረፋቸዉ ስህተት ነበር። የተዘረፉትን ቅርሶች ይዞ ማቆየቱም ስህተት ነበር። ይህ የአዉሮጳ የቅን ግዛት ታሪክ ነዉ። ይህ ታሪካችን በኛ ላይ ጥቁር ጠባሳን ጥሎ ያለፈ፤ በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት ደግሞ ከፍተኛ ችግርን ያስከተለ ነበር። ዛሬ ይህን የመዳብ ቅርስ ስንመልስ የዚህን የታሪክ ምዕራፍ በግልጽነት በእዉነተኛነት እና በራስ አነሳሽነት ትችት መሰረታዊ ዉሳኔ ያሳለፍንበት ነዉ።» የተመዘበረዉ የመቅደላ ቅርሰን በዉሰት?
የጀርመን ጎረቤት ሃገር የሆነችዉ ኔዘርላንድም ባለፈዉ ዓመት በሃገሪቱ የተለያዩ ሙዚየሞች የሚገኙ እና ከተለያዩ አፍሪቃ ሃገራት የተዘረፉ ቅርሳቅርሶችን ከ 60 ዓመታት በኋላ መመልስዋ፤ በሃገሪቱ ለተካሄዱ የባርነት ንግድም ይቅርታ መጠየቋ ተነግሯል። ይህን ተከትሎ በርካታ ከመዳብ እና ከዝሆን ጥርስ የተሰሩ የተለያዩ የቤኒን ስርወ መንግስት ቅርሳ ቅርሶችን አሁንም በተለያዩ ሙዚየሞችዋ ይዛ በምትገኘዉ በብሪታንያ ላይ ቅርሳ ቅርሶችን ለባለቤቶቹ እንድንትመለስ የሚደረገዉ ጫና እየተበራከተ መጥተል።
ብሪታንያ ከናይጀርያ ማለትም ከቤኒን ሥርወ መንግሥት ከተዘረፉ ቅርሶች በተጨማሪ ከኢትዮጵያ የዘረፈቻቸዉ ታሪካዊ ቅርሳቅርሶች በተለያዩ ሙዚየሞችዋ ይገኛሉ። የቅርስ ዘረፋ ጥቅሙ ምን ይሆን? በብሪታንያ የተዘረፉ እና ለንግድ የቀረቡ የኢትዮጵያ ቅርሶችን በመሰብሰባቸዉ የሚታወቁት በለንደን የኢትዮጵያ ቅርስ ማበልፀግያ ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለባቸዉ ደሳለኝፓንክረስት እና ሥራዎቻቸዉ
«ዋናዉ ቁምነገሩ እና ቅርሶችም የሚዘረፉበት ዋናዉ ምክንያት፤ የማንነት መገላጫ እና የታሪክ ምንጮች በመሆናቸዉ፤ ለሃገሪቱም ሆነ ለህብረተሰቡ ታሪካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን በማስገኘታቸዉ ነዉ። የእዉቀት ምንጭ የሆኑትን ቱሪዝም እንዲስፋፋ ጥቅም የሚሰጡትን ቅርሶችን ጉልበተኛ የነበሩት እንደ ኢንጊሊዝ ጣልያን፤ አሜሪካንም ጭምር በጉልበት አልፎ ተርፎ ሰዎችን ባለስልጣናትን ጨምሮ በማማለል ቅርሶችን ከሃገር ይዘርፋሉ። እንደተባለዉ በተለይ እንጊሊዝ በመቅደላ ላይ ባደረገችዉ ወረራ፤ በአጋሰስ እና በዝሆንም ጭምር ጭና በርካታ የኢትዮጵያ ቅርሶችን ዘርፋለች ። እነዚህ ቅርሶች አሁን ብሪታንያ ዉስጥ በሚገኙ ቤተመዘክሮች ዉስጥ ይገኛሉ።»
አቶ አለባቸዉ ከኢትዮጵያ የተዘረፉ ቅርሶች በተለይ በብሪታንያ ሙዚየሞች የሚገኙትን ለማስመለስ ጫና ይደረጋል? የሚያዉቁት ነገር አለ ?በእንግሊዞች ተዘርፈው የነበሩ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቅርሶች ተመለሱ
«በብሪታንያ መንግሥት ላይ ከፍተኛ ጫና ይደረጋል። የኢትዮጵያ መንግሥትም በዚህ ረገድ አጥብቆ ሊሰራበት ጀምሮት ፤ ግን ፍጻሜ ያላገኙ አሉ። በተለይ በመቅደላዉ ጦርነት ወቅት የተዘረፉ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች እንዲመለሱ ለማድረግ ፤የወቅቱ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ሂሩት ፤ ከልዑካኖቻቸዉ ጋር ሆነዉ በተለያዩ የብሪታንያ ሙዚየሞች እየዞር አይተዋል፤ የሙዚየሞቹን የበላይ ሃላፊዎችንም እንዳነጋገሩ መረጃዉ አለኝ። እኔም በእዚህ ጉዳይ ላይ ከዶ/ር ሂሩት ጋር የመነጋገር እድል አጋጥሞኝ ነበር። ዋናዉ ቁምነገሩ እዚህ ላይ ስለታሪክ ስለቅርስ እንቆረቆራለን ወይ ነዉ ጥያቄዉ መሆን ያለበት። የኛ ችግር ፀባችን ከታሪክ ጋር ነዉ። ከዚህ ልንወጣ ይገባል። እናም በእንጊሊዝ የሚገኙ ቅርሶችን ለማስ,ለስ የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብሎ ለመናገር አያስደፍርም።»
አቶ አለባቸዉ ደሳለኝ በብሪታንያ መዲና ከዓመታቶች በፊት ጀምሮ የተዘረፉ እና በንግድ ላይ የሚገኙ ብሎም በግለሰብ እንጅ የሚገኙ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶችን በመሰብሰባቸዉ ይታወቃሉ። ይህን እጃቸዉ ላይ የሚገኝ የሃገሪቱን ቅርስ ወደ ሃገር ለመመለስ ጥረት ከጀመሩም ዓመታት ተቆጥረዋል። በጥንት ጊዜ ከመቅደላ የተዘረፉት እና በተለያዩ የብሪታንያ ሙዚየሞች የሚገኙት የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች ፤ ወደ ኢትዮጵያ ቢመለሱ ሃገሪቱ በተመቻቸ መልክ ለማስቀመጥ አቅሙ ይኖራት ይሆን? ወቅታዊዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካስ ይህን ለመቀበል ዝግጁ ነዉ ወይ ብለዉ ያምናሉ? ለሚለዉ ጥያቄ አቶ አለባቸዉ ደሳለኝ፤
«ዋናዉ ትልቁ ነገር ፖለቲካና ቅርስ የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ።ጀርመን የተዘረፉ ቅርሶችን ለናይጀሪያ መመለስ ጀመረች ቅርስ የማንነት መገለጫ ነዉ ቅርስ ያለፈን ታሪክ የጥበብ አሻራ ማሳያ ነዉ። ቅርስ የስልጣኔ መገለጫ የምስክርነት ቃል የሚሰጥ እማኝ ነዉ። ስለዚህ ይህ የተፈጥሮ እና ሰዉ ሰራሽ ጥንታዊ ቅርስ ወደ ሃገር ገብቶ በጥንቃቄ እንዲቀመጥ መንግሥት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነዉ ብዬ አምናለሁ። ቅርሶች የጋራ መለያዎቻችን የጋራ ሃብቶቻችን ናቸዉ። ቅርሶቻችን በባዕድ ሃገር ሲቀሩ ልንቆጭ ይገባናል። ቅርሶች የአማራ የትግሬ የኦሮሞ ወይም ደግሞ የሌላ ብሄር ብሄረሰቦች የግል ሃብት ሳይሆን የሃገር ሃብት፤ የሃገር ታሪክ በመሆኑ ነዉ። መንግሥት እነዚህን ቅርሶች ቢመለሱ በትክክል ያስቀምጣል ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ይሆናል፤ ምክንያቱም ቅርሶቹ አመቺ እና ሊበላሹ ወይም ለአደጋ እንዳይጋለጡ ሆነዉ መቀመጥ ስለሚኖርባቸዉ ነዉ።»
ቅርስ የአንድን ሃገር ታሪክን ባህልን ጠንቅቆ ወይም አቅፎ ከዘመን ዘመን የሚያሸጋግር ሰነድ ነዉ ሲሉ ምሁራን ይናገራሉ። የአንድን ሃገር ቅርሱ ታሪኩ ሲዘረፍ፤ የራሱ የሆነዉ አሻራ ሲወሰድበት የኔነዉ የሚለዉ ነገር የሚያሳጣ በመሆኑ እያንዳንዱ ዜጋ ቅርሱን ባህሉን የመጠበቅ ሃላፊነት እንዳለበትም ይናገራሉ። አድማጮች በለንደን የኢትዮጵያ ቅርስ ማበልፀግያ ማህበር ዋና ስራስኪያጅ አቶ አለባቸዉ ደሳለኝ ለሰጡን ቃለ ምልልስ በዶቼ ቬለ ስም በማመስገን ሙሉዉን ጥንቅር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ